Tender Detail

Tender Details

  • Company የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ
  • Address ሰሜን ወሎ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 033 331 2751
  • Website
  • Deadline02 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-02 00:00:00
  • Categories Transportation Service And Cargo

የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ የግብርና ግብአት አቅርቦትና የገጠር ፋይናንስ አገልግሎት ቡድን ለ2018/09 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል የአፈር ማዳበሪያ ዳፕ 66595 ዩሪያ 74915 በድምሩ 141510 ኩ/ል (አንድ መቶ አርባ አንድ ሺህ አምስት መቶ አስር) ኩ/ል በዞናችን ባለ ጀምበር ዩኒየን በስሩ ላሉ 42 መሰረታዊ ማህበራት መጋዘን ድረስ ለማጓጓዝ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርተሮች ድርጅቶች

የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ግብ /አቅ/ 001 / 2018

 

የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ የግብርና ግብአት አቅርቦትና የገጠር ፋይናንስ አገልግሎት ቡድን ለ2018/09 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል የአፈር ማዳበሪያ ዳፕ 66595 ዩሪያ 74915 በድምሩ 141510 ኩ/ል (አንድ መቶ አርባ አንድ ሺህ አምስት መቶ አስር) ኩ/ል በዞናችን ባለ ጀምበር ዩኒየን በስሩ ላሉ 42 መሰረታዊ ማህበራት መጋዘን ድረስ ለማጓጓዝ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርተሮች ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ውል ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 30/2018 ዓ/ም ድረስ የሚቆይ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች

1.     የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር/ቢሮ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድና የዘመኑን የመንግስት ግብርለመከፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል)

2.     የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርቲፊኬት/ቲን/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

3.     ተጫራቾች ከ70 ኩንታል በላይ የሚጭኑ ተሸከርካሪዎች የሚያቀርቡ ከሆነና ከፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሠ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ፤

4.     ተጫራቾች የሚያቀርቡት ተሸከርካሪ ከ70 ኩንታል በታች ከሆነ በክልል ትራንስፖርት ቢሮ ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሠ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ

5.     የተሽከርካሪ ዝርዝር /ተ.ቁ፣ የሴለዳ ቁጥር፣ የመኪናው ዓይነትና የመጫን አቅም /የሚያስረዳ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ወይም ከክልል መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የተሰጠ የ2018 ዓ.ም ወቅታዊ የታደሠ ምዝገባ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤

6.     በ2017/2018 ምርት ዘመን ከመንግስት ተቋማት ማዳበሪያ፤ ምርጥ ዘር ፤ እንዲሁም የእርዳታ እህል በማጓጓዝ የመልካም አፈጻጸም ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል

7.     ተጫራቾች በስማቸው የተመዘገቡ እስከ 400 ኩ/ል መጫን የሚችሉ ቢያንስ እስከ 10 እና በላይመኪናዎች በስማቸው የተመዘገበ ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ

8.     ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ 1 እስከ 7 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው

9.     በወቅታዊ የዋጋ መለዋወጥ ምክንያት ነዳጅ ቢጨምር መስሪያ ቤቱ አይጠየቅም

10. የሚጓጓዘውን የአፈር ማዳበሪያ አይነት፣ መጠን የቦታ እርቀት በኪሎ ሜትር ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል

11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዩኒየን ስም የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል በሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ ማግኘት ይቻላል

12. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ወይም /ሲ.ፒ.ኦ ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንከ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ/ሲ.ፒ.ኦ/ በዩኒየን ስም ማስያዝ አለባቸው::

13. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን በአንድ ፖስታ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በማሸግ በጀንበር ዩኒየን ስም ሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ የግብርና ግብአት አቅርቦትና ገጠር ፋይናንስ ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማሰታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማለትም 08/05/2018 ዓ.ም እስከ 16ኛው ቀን ነገር ግን 16ቀን ቅዳሜ በ23/05/2018 ዓ.ም ስለሆነ ወደ ሰኞ ተገፍቶ ማለትም በ25/05/2018ዓ.ም እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ በመምሪያው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ በማስገባት የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈተው በእለቱ በ25/05/2018ዓ.ም በ4፡30 ተኩል ይከፈታል።

14. የተሸከርካሪ የባለቤትነት ማስረጃ ኮፒ ማያያዝ ይኖርበታል።

15. የጨረታ ማስከበሪያው ቢድ ቦንድ ከሆነ ከህጋዊ ቋንቋ ተርጓሚ በማስተርጎም ማቅረብ ይኖርበታል።

16. ዩኒየኑ ጨረታውን እንዲያጫርት ውክልና የተሰጠው የግብርና ግብአት አቅርቦትና ገጠርፋይና ንስ ቡድን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

17. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 331 2751 በመደወል አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ

Save Tender