በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/ መንግስት የዋና አዲተር መ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል፣ የኤሌክትሮኒክስ ኮምፒውተርና ሞባይል/ እና የቢሮ ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/ መንግስት የዋና ኦዲተር መ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/ መንግስት የዋና አዲተር መ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል፣ የኤሌክትሮኒክስ ኮምፒውተርና ሞባይል/ እና የቢሮ ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት -
ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ፣ የአቅራቢነት ሰርተፊኬት፣ የቲን/TIN/ እና የሻት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ኦርጅናሉንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ አቅርበው እንዲመሳከር የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
• ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ ዘወትር በስራ ሰዓት ለተከታታይ 15 ቀናት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የዋና ኦዲተር መ/ቤት ስም በተከፈተው ቢ-አካውንት ቁጥር 1000454358892 ገቢ በማድረግ የባንከ ስሊፕ በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ 100,000 /አንድ መቶ ሺህ/ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መቤት ስም በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
• ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ነጠላ ዋጋ ከነቫት በመጻፍ በሰም በሙጫ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ በማዘጋጀት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ባለት የስራ ቀናት በክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከቀኑ 8:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
• የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ በመክፈቻው ዕለት የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ያለመገኘት የጨረታ መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም።
• እያንዳንዱ ተጫራች ሞልቶ በሚያቀርበው የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ሙሉ ስም፣ ማህተም እና ፈርማ በአግባቡ ማስፈር ይጠበቅበታል፡፡
• ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ራስን ማግለል የተከለከለ ነው።
• ማንኛውም ተጫራች በሚመለከተው የንግድ ስራ ዘርፍ ብቻ መወዳደር አለበት፡፡ ከንግድ ስራ ዘርፍ ውጭ የሚመጣ ተወዳዳሪ ተቀባይነት የለውም።
• ተጫራቾ መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ዋጋ መሙያ ሠነድ መጠይቅ መሰረት ብቻ መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
• የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ቀናት ውስጥ ከመ/ቤቱ ጋርየውል ግዴታ መግባት አለበት።
• አሸናፊው ድርጅት ያሸነፉዋቸውን ዕቃዎች በሙሉ በገቡት ውል መሰረት እስከ መ/ቤታችን ድረስ አቅርቦ ንብረት ክፍል ገቢ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታ አሸናፊ ከተገለፀበት ቀን እንስቶ ለሰላሳ/30/ ቀናት ይሆናል፡፡
• መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ
ለበለጠ መረጃ
ስልክ - ቁ 09-17-82-21-28 /09-01-40-42-93
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/ መንግስት የዋና ኦዲተር መ/ቤት
