Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian sugar industry group Omo kuraz 1 & 3 Sugar Factory (በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት)
  • Address አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ ተዘንአ አጠቃላይ ሆስፒታል በሚያስገባው አስፓልት ከጦር ሃይሎች ወደ ዘነበ ወርቅ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ 3 ቁጥር ማዞሪያ / ቶታል ገባ ብሎ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ ላይ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 251910120628
  • Website
  • Deadline29 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-29 00:00:00
  • Categories Vehicle tire , Machinery Spare Parts

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-1 እና 3 ስኳር ፋብሪካዎች ያገለገሉ የተለያየ ሳይዝ ያላቸው የቀላል ተሽከርካሪዎች እና የከባድ ማሽነሪ ጎማዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

Ethiopian sugar industry group Omo kuraz 1 & 3 Sugar Factory (በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት)


የሚወገዱ ንብረቶች ሽያጭ

ሶስተኛ ዙር የወጣ ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አሽጨ/003/ኦኩስፋ/እና3/2018

 

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-1 እና 3 ስኳር ፋብሪካዎች ያገለገሉ የተለያየ ሳይዝ ያላቸው የቀላል ተሽከርካሪዎች እና የከባድ ማሽነሪ ጎማዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

1.     ማንኛውም ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይም ህጋዊ የታደሰ የቀበሌ መታወቅያ ሰነድ/መረጃ ማቅረብ አለባቸው።

2.     ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶች የሚገኙበት አድራሻ፡- ከልል በምእራብ ኢትዮጵያ ቤንች ማጂ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ እና ከልል ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ወረዳ ሳላማጎ ወረዳ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር-1 ስኳር ፋብሪካ ግቢ ነው።

3.     ጨረታው በቀን 21/5/18 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል። ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሽገ ኢንቨሎፕ (ፖስታ) በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል። በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን 21/5/18 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።

4.     ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በሃርድ ኮፒ እና 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በሶፍት ኮፒ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-8:00) ከታች በተራ ቁጥር 5 እና 6 በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

5.     ለሽያጭ የቀረቡ እቃዎች ወይም ንብረቶችን ዝርዝር የያዘው መደበኛ የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት የመወዳደሪያው ሰነድ የሚገባበት እና ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ፡- ኦሞ ኩራዝ ቁጥር -1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ ተዘንአ አጠቃለይ ሆስፕታል በሚያስገባው አስፓልት ከጦር ሃይሎች ወደ ዘነብ ወርቅ በሚወስደው መንገድበተለምዶ 3 ቁጥር ማዞርያ /ቶታል ገባ ብሎ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ ላይ ስልክ ቁጥር 09-63-44-28-82 እና 09-13-54-47-31 አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ

6.     በተጨማሪ የጨረታ ሰነድ ለመሸጥ ብቻ የሚያገለግል የሻጭ አድራሻ ኦሞ ኩራዝ ስኳር ፍብሪካ ቁጥር-- እና 3 ስልክ ቁጥር 09-16-17-08-34 ኩራዝ

7.     ለሽያጭ የቀረቡ ዕቃዎች ርክክብ የሚፈፀመው ቦታ በኦሞ ኩራዝ ቁጥር-ኣና3 ስኳር ፋብሪካ ግቢ ውስጥ ነው።

8.     ብቁ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ጥቅል ዕቃዎች ቀጥሎ የተመለከተውን የብር መጠን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

ጥቅል-1 (ሎት-1) የተሸከርካሪ የጎማ ሽያጭ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)

ጨረታው ጸንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 (ስልሳ) ቀናት ነው።

ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት ኩራዝ

Save Tender