የጨረታ ቁጥር ጉ/ክ/ከ/ወ/3/ፋይናንስ ጽ/ቤት 002/2018 ዓ.ም የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጻም ይፈልጋል።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002
የጨረታ ቁጥር ጉ/ክ/ከ/ወ/3/ፋይናንስ ጽ/ቤት 002/2018 ዓ.ም የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጻም ይፈልጋል። 1ኛ ሎት 1. የትራንስፖርት አገልግሎት 2ኛ ሎት 2. የደንብ ልብስ
በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
1. የሚወዳደሩበት የንግድ ዘርፍ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመንግሰት ዕቃ ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችልና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
2. የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ፤ ሎት1/ ትራንስፖርት 10,000 ( አስር ሺህ ብር) 2.የደንብ ልብስ 3,000( ሶስት ሺህ) ብር መያዣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ በጉ/ክ/ከ/ወ/3 ፋይናንስ ፅ/ቤት በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል።
3. ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ከመ/ቤታችን ጋር የውል ማስከበሪያ ላሸነፉባቸው እቃዎች የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተመሰከረ / cpo/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡ ይህ ባይሆን ግን በጨረታ ያስያዙት ሲፒኦ በቀጥታ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
4. የሚያቀርቡት የዕቃው ዋጋ በሁለት ፖስታዎች ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በመምጣት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን 04:30 በወረዳው አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል የመክፈቻው ቀን በዓል ወይም እረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
6. የጨረታው ዝርዝር የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100ብር / አንድ መቶ ብር / በመክፈል ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 መውሰድ ይችላሉ።
7. ተጫራቾች ለመወዳደር በመረጡት ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በወረዳው ጽ/ቤት መቅረብ አለባቸው።
8. የሚያቀርበው የእያንዳንዱ ዕቃ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል።
9. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የአቅራቢነት ማስረጃ ኮፒ የሚታይ መሆን አለበት።
10. አቅራቢ ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ንብረት ክፍል መድረስ ይኖርበታል።
11. አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ አስተዳደሩ ባወጣው ጨረታ ላይ ከውል በፊት የእቃውን ብዛት 20% መጨመርና መቀነስ ይችላል እንዲሁም ከውል በኋላ ደግሞ 25% የዋጋውን መጨመር ይችላል፡፡ በጨረታ መወዳደሪያ የሚቀርብ ዋጋ ለስድስት ወር ፀንቶ ይቆያል።
12. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ማብራሪያ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0111222600 መደወል ይቻላል።
14. የእያንዳንዱ ዕቃ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል።
ማሳሰቢያ፡-ለጥቃቅን እና አነስተኛ ተጫራቾች ቅድሚያ እንሰጣለን በተጨማሪም መወዳደር የሚችሉት አምራች በሆኑበት የንግድ ዘርፍ ብቻ ነው።
አድራሻ፡- ከመነን ሽሮሜዳ በሚወስደው መንገድ ፀሐይ ጮራ ት/ቤት ፊት ለፊት
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
