Tender Detail

Tender Details


በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ የቀራንዮ መ/ዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን መግዛት ስለሚፈልግ በወጣው ግልፅ ጨረታ ላይ ተመስርቶ በተዘጋጀው ጨረታ መሰረት ሎት አንድ አላቂ የቢሮና የትምህርት ዕቃዎች፣ ሎት ሁለት የደንብ ልብስ፣ ሎት ሶስት አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት አራት ቋሚ እቃዎች፣ ሎት አምስት የኤሌክትሮኒከስ አላቂ እና ቋሚ እቃዎች፣ ሎ

በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የቀራንዮ መ/ዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


ለ2ኟ ዙር የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 003/2018

በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ የቀራንዮ መ/ዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን መግዛት ስለሚፈልግ በወጣው ግልፅ ጨረታ ላይ ተመስርቶ በተዘጋጀው ጨረታ መሰረት ሎት አንድ አላቂ የቢሮና የትምህርት ዕቃዎች፣ ሎት ሁለት የደንብ ልብስ፣ ሎት ሶስት አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት አራት ቋሚ እቃዎች፣ ሎት አምስት የኤሌክትሮኒከስ አላቂ እና ቋሚ እቃዎች፣ ሎት ስድስት የሕትመት ሥራዎች፤ ሎት ሰባት አላቂ የስፖርት ዕቃዎች፣ ሎት ስምንት አላቂ እና ቋሚ የላብራቶሪ እቃዎች፣ ሎት ዘጠኝ የተለያዩ አይነት መጽሐፍቶች፣ሎት እስር የትራንስፖርት እና የጭነት አገልግሎት የተለያዩ ቦታዎች እና ሎት አስራ አንድ የማባዣ ማሽን፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ ፕሪንተር፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ ሲስተም ዩኒት፣ ጄኔሬተር ጥገና እና ሰርቪስ ሲሆኑ በዚህ መሰረት እያንዳንዱ ተጫራች የሚከተሉትን ነጥቦች በመረዳት የጨረታ ሰነዳቸውን በዚህ መመሪያ መሰረት አሟልተው እንዲያቀርቡ ያስፈልጋል፡፡

1. ተጫራቾች የዘመኑን የግብር የከፈሉ፣አግባብነት ያለው የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም ከአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስና አኮኖሚ ልማት ቢሮ በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስከር ወረቀት የታደሰ ማቅረብ የሚችሉ፣ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ታከስ ከሊራንስ ሰርተፍኬት፣ ቲን ነምበርእና ጨረታን ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስከር ወረቀት ከጨረታው ሰነድ ጋር እያይዛችሁ ማቅረብ ይኖርባችዋል፡፡

2. የጨረታ ሰነዱ በፖስታ ታሽጎ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ቢሮ ቁጥር 34 የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ መረከቢያ ሰዓት ከመድረሱ በፊት መግባት ይኖርበታል፡፡

3. ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት ከ ከተዘረዘሩት የጨረታ ዓይነቶች በሙሉ ወይም በከፈል መጫረት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የጨረታ ዓይነት ውስጥ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች! መጓጓዣዎች፣ የጥገና እና ሰርቪስ ሥራዎች ቫትን ጨምሮ የእያንዳንዱን ዋጋ በግልፅ ማስፈር አለባቸው፡፡

5. ጨረታውን ለሚወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ 9,000 ብር፣ ለሎት ሁለት እና ሎት ሶስት ለእያንዳንዱ 8,000 ብር፣ ለሎት አራት እና ለሎት አምስት ለእያንዳንዱ 7,000 ብር፣ ለ‐ት ስድስት 2,000 ብር፣ ለሎት ሰባት 7.500 ብር፣ ለሎት ስምንት 8,000 ብር፣ ለሎት ዘጠኝ 7.000፣ ለሎት አስር እና አስራ እንድ 3.000 CPO የሚመለስ በመሰሪያ ቤቱ ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባችዋል፡፡

6. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመከፈል ይሀ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከቢሮ ቁጥር 04 መግዛት የሚችሉ ሲሆን መ/ቤቱ የሸጠውን የመደበኛ የጨረታ ሰነድ ከፍት ቦታዎች ተሞልቶና እያንዳንዱ ገፅ ላይ ተፈርሞና በማህተም ተረጋግጦ መመለስ ይኖርበታል፡፡

7. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት ከሥራ ሂደቱ ጋር በሚገባው ውል መሰረት ዕቃዎቹን እንዲያሰገባ ሲታዘዝ አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ በጠቅላላው ባሸነፈው ዋጋ 10% የሚመለስ በመስሪያ ቤቱ ስም CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

8. በዚህ ጨረታ ላይ የሚቀርብ ማንኛውም የመወዳደሪያ ዋጋ ቢያንስ ለ60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡

9. የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

10. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ናሙና ለተጠየቁት ዕቃዎች ከጨረታው ማብቂያ ሰዓትና ቀን በፊት ናሙናዎቹን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

11. የመጫረቻ ሰነድ የማስረከቢያ የመጨረሻው ቀን ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የሥራ ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡ የጨረታው ሳጥን በ11ኛው የሥራ ቀን በ3፡00 ተዘግቶ (ታሽጎ) በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የት/ት ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

12. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት (ድርጀቶች) ማሸነፉ እንደተገለፀለት በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውሰጥ ቀርቦ ውል ካልፈፀመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያሰያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ሆኖ መ/ቤቱ እንደ ምርጫው 2ኛ እና 3ኛ የወጣውን ተወዳዳሪ ለጋብዝ ይችላል፡፡

13. በመ/ቤታችን በወጣው ጨረታ መሰረት ያለዘርፉ ለመወዳደር ሰነዱን ሞልቶ ያቀረበ ድርጅት ከጨረታው ይሰረዛል፡፡

14. መ/ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በድርጅቱ የሥራ ቦታ በመገኘት የዕቃዎችን ጥራትና የድርጅቱን አቅም ለመገምገም ቢፈልግ ድርጅቱ የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡

15. አልፎ አልፎ የተመለከቱት የዕቃዎች ልዩ መለያ በጠያቂ መ/ቤቶች ፍላጎት መሰረት ብቻ የዕቃውን የጥራት ደረጃ ለማመልከት የቀረበ ስለሆነ ማንኛውም ተጫራች ተመሳሳይና ከነዚህ የተሻሉ ዕቃዎችን ማቅረብ ይችላል፡፡

16. ለውድድር የሚቀርበው የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ሰነድ በተለያየ ፖስታ ታሽጎ አብሮ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

17. በመ/ቤታችን ለዕቃ ጥራት ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ በመሆኑ ተወዳዳሪዎች የተሻለ ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች

18, ማንኛውም ተጫራች ከዚህ መመሪያ ውጪ ሙስና እና ከሙስና ጋር የተያያዙ ድርጊቶችን ቢፈፅም ወይም በሕገ ወጥ መንገድ ለማሸነፍ ቢሞክር ወዲያውኑ ከጨረታው ይሰረዛል፣ ያስያዘውም ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል፡፡

19. ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ጨረታው ላይ መሳተፍ የሚችሉት በሚያመርቱት ምርት ላይ ብቻ መወዳደርይችላሉ፤ በተጨማሪም አምራች መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

20. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 251 118 35 74 84/+251 118 35 74 76 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- ከሆላንድ ኤምባሲ ጀርባ ቀራንዮ መ/ዓለም ቤተ ክርስቲያን መግቢያ(ቀራንዮ አደባባይ)

በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ትምህርት መምሪያ የቀራንዮ መ/ዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

Save Tender