አምቦ የገ/ህ/ሥራ ማህበራት ዩኒየን የ2018/2019 ዓ.ም የምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያ በሽገር ከተማ ታጠቅ ኢንዱስትሪ መንደር መጋዘናችን በመጫን በምዕራብ ሸዋ ዞን በዩኒየኑ የሥራ ክልል ሥር ላሉት የህብረት ሥራ ማህበራት ለማጓጓዝ ይፈልጋል።
አምቦ ገበሬዎች ሕብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ
ለአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዝ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
አምቦ የገ/ህ/ሥራ ማህበራት ዩኒየን የ2018/2019 ዓ.ም የምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያ በሽገር ከተማ ታጠቅ ኢንዱስትሪ መንደር መጋዘናችን በመጫን በምዕራብ ሸዋ ዞን በዩኒየኑ የሥራ ክልል ሥር ላሉት የህብረት ሥራ ማህበራት ለማጓጓዝ ይፈልጋል።
ስለዚህ
በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዴታዎች የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፣ ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባቸው መሠፈርቶች፡-
1. በ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ፎቶ ኮፒ ሆኖ በጀርባው የድርጅታችሁ ማህተም ያረፈበት ማቅረብ የሚችሉ ፣
2. የማጓጓዣ ታሪፍን በተመለከተ አንዱን ኩንታል ከሚጫንበት መጋዘን እስከ መሠረታዊ የህብረት ሥራ ማህበራት የሚያጓጉዝበትን ዋጋ መስጠት አለባቸው፣
3. አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።
4. ተጫራቾች ያላቸው የመኪና ብዛት ከስድስት (6) ያላነሰ እና የመጫን ችሎታ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ለ2018 ዓ.ም የታደሰ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
5. ተጫራቾች ለጨረታ በሚቀርቡበት ወቅት ቢያንስ ከሁለት ዓመት ያላነሰ የቅርብ ጊዜ /የ2016 እና 2017 ዓ.ም/ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፣ ከዩኒየናችን ጋር የሰሩ ከሆነም የዩኒየናችን ድጋፍ የ2016 እና 2017 ዓ.ም በጽሁፍ ማቅረብ አለባቸው።
6. ተጫራቾች ከዚህ በፊት ከዩኒየናችን ጋር ሰርተው ከሆነ ወጪ ያደረጉትን ንብረት በጠቅላላ ገቢ ያላደረጉ ከሆነ በጨረታው ላይ መወዳደር አይችሉም።
7. ከተወዳደረበት የአፈር ማዳበሪያ ብዛት ጋር የሚመጣጠን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 5% CPO ወይም Bid bond ማቅረብ አለበት። የጨረታው ማጣራት እንዳበቃ ለተሸናፊዎች ሲመለስላቸው አሸናፊዎች ግን ሥራውን በተዋዋሉት መሠረት ሲያጠናቅቁ ይመለስላቸዋል።
8. የማራገፈያ ጣቢያዎቹን እና የማዳበሪያውን ብዛት የሚገልጽ ሰነድ ከዩኒየኑ ገበያ መምሪያ ክፍል ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ሰዓት፣ የማይመለስ 6,000 ብር ባንክ በማስገባት ዘወትር በዩኒየኑ ሥራ ሰዓት የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
9. ጨረታውን፤ ያሸነፈ፤ አካል ያሸነፈበትን ጠቅላላ የጭነት ዋጋ 1% በCPO /performance Bond/ ማስያዝ የሚችል።
10. የአፈር ማዳበሪያውን የሚያጓጉዝበትን ዋጋ በሁሉም ማህበራት ላይ በኩንታል መስጠት ተጫራቾቹ በሁለም ማህበራቾች ላይ ዋጋ የማይሰጡ ከሆነ ከውድድሩ ውጪ ይሆናሉ፡፡
11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 ተከታታይ አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ22ኛው ቀን በ4:30 ሰዓት ጠዋት ታሽጎ በ5:00 ሰዓት ጠዋት በዩኒየኑ ቦርድ ክፍል ይከፈታል። 22- ቀን የሥራ ቀን ካልሆን በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
12. ተጫራቾች ተወካዮቻቸው በጨረታው መክፈቻ ላይ ለመገኘት ከድርጅቱ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተወዳዳሪዎች በሙሉ ባይገኙም በተገኙት ፊት ጨረታው ይከፈታል።
13. ተወዳዳሪዎች የፋይናንስ እና የቴክኒክ ዶክመንቶችን ለየብቻ በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
14. በተቀራራቢ ጣቢያዎች ላይ የተጋነነ የዋጋ ልዩነቶችን ለማስታረቅ ሲባል ዩኒየኑ የራሱን አማራጭ የመውሰድ መብት ይኖረዋል። ዩኒየኑ በትራንስፖርት ጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
15. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ +251112609101/+2511123633990 መጠቀም ይቻላል።
አምቦ ገበሬዎች ሕብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ
