ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ሴንተር ኃ/የተ/የግ/ማ የሚከተሉትን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ይፈልጋል።
ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ሴንተር ኃ/የተ/የግ/ማ
የጨረታ ማስታወቂያ
ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ሴንተር ኃ/የተ/የግ/ማ የሚከተሉትን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ይፈልጋል።
1. 7 ስማርት ስልኮች (Samsung Galaxy A56 5G):
2. 2 የካሜራ ላይቶች (Amran 300x Light with stand)
3. ኤክስተርናል ስቶሬጅ (2×2TB Samsung SSD)
4. 2 የብላክ ማጅክ ካሜራ ባትሪዎች (6k Camera Battery) እንዲሁም
5. ሚሞሪ ካርድ (Memory 12/256GB)
ስለሆነም-
የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያላቸው።
ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡-
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) ብር 10,000.00 አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ሴንተር በሚል አድራሻ በባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፤
ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ ማህተም በማድረግ ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ቲን ነምበር በአንድ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናል የጨረታ ሰነድ እና በሌላ ፖስታ ኮፒ በማድረግ በፖስታው ላይ ኮፒና ኦርጅናል ብለው በመጻፍ ሁለቱን ፖስታዎች በአንድ ፖስታ ተደርጎ ድርጅቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ማለትም ጥር 2/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሦስት ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጥር 7 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
በጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ መኖር የለበትም፤ ነገር ግን ሥርዝ ካለው ፓራፍ መደረግ አለበት።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የጨረታው አሸናፊ በ 10 ቀናት ዉስጥ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል።
ከዚህ በላይ ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ መሰረት ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ፤ ቦሌ መድሃኒዓለም ቤተ-ክርስቲያን ፊት ለፊት አውሎ ቢዝነስ ሴንተር 7ተኛ ፎቅ።
(+251) 116 61 61 85
ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ሴንተር ኃ/የተ/የግ/ማ
