የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለታላቁ አንዋር መስጅድ አገልግሎት የሚውል ጀነሬተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ መለያ ቁጥር AAM 06/2018
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለታላቁ አንዋር መስጅድ አገልግሎት የሚውል ጀነሬተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
• ሎት 1 የጀነሬተር ግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር ….. 50,000
በዚሁ መሠረት ተጋባዥ ተጫራች ድርጅቶች-
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀትና የቫት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000050280873 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የመጫረቻ ሰነዱ በአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ቢሮ ቁጥር 413 ለተከታታይ 8 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት አርብ ዝግ ሆኖ ቅዳሜ ክፍት ነው) መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የቴክኒካልና ዶክመንት አርጅናል እና 1 ኮፒ እና ፋይናሻል ዶክመንት ኦርጅናል እና 1 ኮፒ በተለያየ ፖስታ ታሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች የነጠላ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ልዩ ስሙ ጦር ሀይሎች በሚገኘው ምከር ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 8ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ማስገባት አለባቸው። የጨረታው ቴክኒካል ዶክመንት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ምክር ቤቱ በሚያመቻቸው አዳራሽ 5፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
5. የጀነሬተሩ ዝርዝር መግለጫ በፅሁፍ እና በፎቶ የተደገፈ ካታሎግ ከቴክኒካል ዶክመንት ጋር አብሮ መቅረብ አለበት፡፡
6. ተጫራቾች በአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ስም በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ወይንም ለ60 ቀን የሚቆይ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው።
7. በጨረታ ሰነዱ ላይ በእያንዳንዱ ገጽ የድርጅቱ ክብ ማህተምና ፊርማ ማድረግ | እንዲሁም ዋጋ የሚሞላው በም/ቤቱ ዋጋ ማቅረቢያ ብቻ ሆኖ ስርዝ ድልዝ ቢያጋጥም በፊርማ ማረጋገጥ ይኖርበታል።
8. 8ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ (አርብን ጨምሮ) በቀጣዩ የመንግሥት የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት መሠረት ጨረታው ይከፈታል፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች በግዴታ ውስጥ የተካተቱትን ሕጐች ማክበር የሚችል መሆን አለበት።
10. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች ምከር ቤቱ ቅጥር ግቢ አምጥቶ የሚያስረክብ መሆን አለበት፡፡
11. ምክር ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. ጨረታው ለ60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 09 22 73 16 27 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት
