በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር በ10ኛ ዕዝ ግዥ ቡድን በበጀት ዓመቱ የቀላል የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን እና የወታደራዊ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር የ10ኛ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር – 10ኛ ዕዝ ብ/ግ/ጨ/01/2018
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር በ10ኛ ዕዝ ግዥ ቡድን በበጀት ዓመቱ የቀላል የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን እና የወታደራዊ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. በዘርፉ የተሠማሩና ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም ለተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 “ለ” በተገለፀው አድራሻ መሰረት የማይመለስ ብር 100.00 /መቶ ብር/ በመክፈል የተሟላ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች በተራ ቁጥር 7 ለ በተገለፀው አድራሻ መሰረት የመጨረሻው የጨረታ ማስገቢያ ቀን ገደብ ከመጠናቀቁ በፊት ጥር 15 ቀን 2018 እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የመጫረቻ ሰነዳችሁን ዋናውን እና ኮፒውን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ለጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ከታወቀ ባንክ ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ ከመጫረቻ ሰነዳችሁ ጋር አያይዛችሁ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተ/ቁጥር 7 “በተገለፀው አድራሻ የመጨረሻው የጨረታ ማስገቢያ ቀነ ገደብ እንደተጠናቀቀ ጥር 15 ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
4. የዕቃዎች ማስረከቢያ ቦታ ጎንደር አዘዞ ከተማ በሚገኘው የ10ኛ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ግምጃ ቤት ሲሆን የትራንስፖርትና ማራገፊያ ወጪ በአቅራቢዎች የሚሸፈን ይሆናል፡፡
5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት የዕቃዎቹን ናሙና ወይም ካታሎግ ከጨረታ ሰነዶቻችሁ ጋር ይዛችሁ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።
6. መ/ቤታችን እንደ አስፈላጊነቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
7. ለተጨማሪ ማብራሪያና ጨረታ ሰነድ ማስገቢያ፦
ሀ. ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ፡
የ10ኛ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ (ጎንደር-አዘዞ ከተማ)
ስልክ :-0912 83 50 10 / 0911 11 00 84 / 0912 94 60 99
ሐ. ሰነዱ ወጪ የሚሆንበት አድራሻ
7ለ ይመልከቱ
ለ. ጨረታ ሰነድ ማስገቢያ
10ኛ ዕዝ ጠ/መምሪያ ጎንደር-አዘዞ
ስልክ 0912 83 50 10 / 0911 11 00 84 / 0912 94 60 99
ቢሮ ቁጥር 03 (ግዥ ቡድን)
መ. ጨረታ የሚከፈትበት አድራሻ፡-
በ10ኛ ጠ/መምሪያ ቢሮ በዋናው አዳራሽ
በኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር የ10ኛ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
