በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሥር የሚገኘው የወረዳ 9 ኳስ ሜዳ ጤና ጣቢያ የሚያስፈልጉትን አላቂ የፅህፈት መሣሪያ የፅዳት ዕቃዎች የደንብ ልብስ ጨርቆች መድሃኒቶችና ሪኤጀንቶችን ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 9 ኳስ ሜዳ ጤና ጣቢያ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 002/2018ዓ/ም
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሥር የሚገኘው የወረዳ 9 ኳስ ሜዳ ጤና ጣቢያ የሚያስፈልጉትን አላቂ የፅህፈት መሣሪያ የፅዳት ዕቃዎች የደንብ ልብስ ጨርቆች መድሃኒቶችና ሪኤጀንቶችን ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
ስለሆነም ይህንን የጨረ ማስታውቂያ አውጥቶዋል። በመሆኑም በዚህ ጨረታ ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛወም ህጋዊ ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርት አሟልቶ ለጨረታው መወዳደር ይችላል።
1. በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉ።
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገቡ።
3. አቅራቢዎች በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተዘገበና በራብሳይት የሚረጋገጥ የሙያ ብቃት ያላቸው።
4. የሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ከቫት ጋር የተሰላ / ተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለበት
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ከጨረታው ፖስታ ጋር አብረው ማስገባት አለባቸው።
• ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል በወረዳ 9 ኳስ ሜዳ ጤና ጣቢያ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በኩል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
• ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ሰነዶችን ለየብቻ በማድረግ ማስታወቂያው ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቤሮ በመገኘት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
• ለተጫራቾች ጨረታው እንደተጠናቀቀ ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ
➢ ሎት 1፡ መድሀኒቶችና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች 50,0000 (0.5) (ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ)
➢ ሎት 2፦ አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች 2,500 (0.5) (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ)
➢ ሎት 3፦ የደንብ ልብስ…5000 (0.5) (አምስት ሺህ ብር ብቻ) ሎት
➢ 4፦ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች……5000 (0.5) (አምስት ሺህ ብር)
➢ ሎት 5፦ የተለያዩ ከፍሎች ጥገና ስራ…7500 (0.5) (ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር)
➢ ሎት 6፦ የደንብ ልብስ ስፌት…… 6000 (0.5) (ስድስት ሺህ ብር)
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ ከ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታዛቢዎች ባሉበት የጨረታ መቀበያ ጊዜ ያበቃ መሆኑን የሚገልፅ ቃለ ጉባኤ በመያዝ ተዘግቶ በዛው ዕለት እና ሰዓት 4፡30 ላይ የመከፈቻ ቃለ ጉባኤ ተይዞ ሲታሸግ የነበሩ ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል። በዚህ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲገኙ ይጋበዛሉ፤ ባይገኙ ግን የጨረታ መዝጊያውም ሆነ የመክፈቻ ቀኑ ወይም ሰዓቱ የማይራዘም መሆኑን እናሳስባለን።
6. አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ የውሉን ዋጋ 10% (አሥር በመቶ) በውል ማስከበሪያነት ለመንግስት መስሪያ ቤቱ ማስያዝ አለባቸው።
7. ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች በጥራት ደረጃ አስተማማኝነቱን የጠበቀ ናሙና ከጨረታው በፊት ማቅረብ አለባቸው።
8. ማንኛውም የጥቃቅን ተጫራች ካደራጃቸው አካል አምራች መሆናቸውን የሚገልፅ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-275-90-75 ሊያገኙን ይችላሉ።
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መሣለሚያ ወደ ኮልፌ አጠና ተራ በሚወስደው መንገድ በለስ ሆቴል ፊት ለፊት ወይም ባለሶር ህንፃ በስተጀርባ በኩል ወረዳ 9 ኳስ ሜዳ ጤና ጣቢያ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት
የወረዳ 9 ኳስ ሜዳ ጤና ጣቢያ
