የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ዶዘርና ኤክስካባተር ባለጎማ በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
Gullele Botanic Garden (ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2018
የዶዘርና ኤክስካባተር ባለጎማ ኪራይ ጨረታ
የተጫራቾች መመሪያ
1. ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር አጠናቀው የከፈሉ ስለመሆናቸው እና ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
2. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
3. ተጫራቾች በዘርፉ ተሰማርተው የሰሩበትን የስራ ልምድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
4. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3,000.00 (ሶስት ሺህ ብር) በባንከ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተደራጅተው ለሚጫረቱ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያው እና የውል ማስከበሪያው ሲፃፍ በተደራጁበት ዘርፍ መፃፍ አለባቸው፤
5. ተጫራቾች በቀረበው ሰነድ መሰረት አሸናፊ ተለይቶ ጨረታውን ስለማሸነፉ በማስታወቂያ ይፋ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ቀናት ውስጥ ያቀረበውን ዋጋ ገቢ በማድረግ ውል ካልተዋዋለ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤
6. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ የማይመለስ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሣ ብር ብቻ) በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፤
7. ተጫራቾች ድርጅቱ በሚያወጣው የጉብኝት ፕሮግራም መሰረት የዶዘርና ባለጎማ ኤክስካባተር አገልግሎቱ የሚፈለግበት ቦታው ድረስ በመሄድ ተዘዋውረው ማየት ይችላሉ፤
8. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ በመንተራስ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፤
9. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ሲያቀርቡ በሰነዱ ላይ ተፈርሞበትና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነዶች አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በማዘጋጀት ለየብቻው በታሸገ ካኪ ፖስታ በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
10. ከላይ የተገለፀውን መስፈርት በማሟላት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 የጨረታው ሰነድ የሚሸጥ ሲሆን፣ በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 የመስከ ጉብኝት የሚደረግበት ቀን ሆኖ፣ ነገር ግን በዚሁ ዕለት የጨረታ ሰነድ የሚሸጥ ይሆንና በ11ኛው ቀን ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ጠዋት 4፡00 ሰዓት የመወዳደሪያ ሰነድ ማስገባት የሚቻል ሲሆን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ ወይም የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፤
11. ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011547226 ደውለው ያነጋግሩ፡፡
ህንፃ ቁጥር- 2 1ኛ ፎቅ ላይ
አድራሻ፡- ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 በፅዮን ሆቴል 800 ሜትር ገባ ብሎ
ልዩ ስሙ አጣሪ ሰፈር ባለው የማዕከሉ ጽ/ቤት
ልዩ ስሙ አጣሪ ሰፈር ባለው የማዕከሉ ጽ/ቤት የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል
