Tender Detail

Tender Details

  • Company የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ጽ/ቤት
  • Address አማራ ኢትዮጵያ, Phone: 058 2204516
  • Website
  • Deadline21 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-21 00:00:00
  • Categories Animals , Animal Feed And Supply

የጨረታ ቁጥር እዓሀቢሮ 132/2018 የተስያዩ የእንስሳት መኖ ዘር ግዥ በአማራ ከልል እንስሳትና ዓሳ ሀብት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በሪስቶር ፕሮጀከት በጀት በተገኘ ድጋፍ ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ የእንስሳት መኖ ዘር አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር እዓሀቢሮ 132/2018 የተስያዩ የእንስሳት መኖ ዘር ግዥ በአማራ ከልል እንስሳትና ዓሳ ሀብት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በሪስቶር ፕሮጀከት በጀት በተገኘ ድጋፍ ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ የእንስሳት መኖ ዘር አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የእቃው ዝርዝር

ሎት 2 በሪስቶር በጀት የመኖ ዘር አቅርቦት

ሎት 3 የችግኝ ጣቢያ ቁሳቁስ

1. በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

2. የፌዴራል ግብርና ባለስልጣን ወይም የአብከመግብርና ባለስልጣንያወጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉና ከባለስልጣኑ የሰነድ ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ።

3. የሚገዙ የመኖ ዘር አይነት እና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ የመኖ ዘር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ/ እና የችግኝ ጣቢያ ቁሳቁስ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከባንከ በተመሰከረሰት ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ባህርዳር ከተማ በሚገኘው የአብከመ ግብርና ቢሮ ቁጥር 69 የማይመለስ ብር 500.00 / አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

6. የመወዳደሪያ ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው መሰረት በእያንዳንዱ እቃ ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

7. ቴከኒካል ፕሮፖዛል እና የዋጋ ማቅረቢያ /ፋይናሻል ፕሮፖዛል/ እያንዳንዱን ለየብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፤

8. ከቴከኒካል ፕሮፖዛል ጋር አብሮ በፖስታ መታሸግ ያለባቸው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማስረጃ፣ የመጫረቻ ሰነድ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ቀናት፣ አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በስንት ቀን ውስጥ አጠቃሎ ማስረከብ ያለበት መሆኑን የሚገልጽ ጽሁፍ፣

9. ፋይናንሻል ፕሮፖዛል ጋር አብሮ በፖስታ ማሸግ ያለብዎት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብቻ ነው።

10. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልከ ቁጥር 0582204516 /0582206479 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

11. ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ተዘግቶ በዚያው እለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ - በስልክ ቁጥር 058 220 4516 ወይንም 058 220 6479

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የእንስሳትና

ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት

Save Tender