Tender Detail

Tender Details

  • Company የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት
  • Address በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ከብሩክ ህንፃ ፊት ለፊት ቴሌ አጠገብ ከተሰራው አዲሱ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ህንፃ ውስጥ 1ኛ ፎቅ ወደ ቀኝ ሲታጠፉ የወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0113301548
  • Website
  • Deadline20 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-20 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing , Machinery , Furniture , Electronics Materials , Camera

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለከተማው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቋሚ እቃዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ባላቸው አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር-005/2018

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለከተማው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቋሚ እቃዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ባላቸው አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

•        ሎት-1 ሞንታርቦ ከነአክሰሰሪው

•        ሎት-2 ካሜራ ከነአክሰሰሪው

•        ሎት-3 የቄራ ማጠቢያ ማሽን

•        ሎት-4 ቶታል ስቴሽን

•        ሎት-5 ፈርኒቸር ግዥ (ሜንሽ ወንበር)

በዚህም መሰረት፡- ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡

1.     ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ (ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2.     ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ስለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NUMBER) ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡

3.     ተጫራቾች በፌዴራል መንግሥት የግዥ ስርዓት በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ e-GP ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።

4.     ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ በወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ፤ CPO ሎት 1/40,000፣ ሎት-2/ 40,000፣ ሎት 3/ 50,000፣ ሎት 4/ 50,000 እና ሎት 5/ 50,000 ብር በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5.     ተጫራቾች የሚወዳደሩበት እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ከወ/ጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ግ/ን/አስ/ዋና/ሥራ ሂደት ክፍል ቀርቦ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

6.     ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 የጨረታው ሳጥን ታሽጎ በዚሁ ቀን 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

7.     ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ሁለት ኮፒውን በተናጠል ለይቶ በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቮሎፕ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

 

–       ማሳሰቢያ ፡ ፅ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

–       በጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታው ከመከፈት አያስተጓጉልም።

–       መ/ቤቱ ከሸጠው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ ሞልቶ መወዳደር አይቻልም።

–       የጨረታ ማስታወቂያውንና የጨረታ ሰነዱ የሚጠይቀውን ዝቅተኛ መስፈርት የማያሟሉ ተጫራቾች ወይም አቅራቢዎች ከጨረታው ውጪ ይደረጋሉ።

–       የጨረታውን መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ብሔራዊ የህዝብ በዓል ከሆነ ቀጣይወዳለው የሥራ ቀን ይተላለፋል።

 

ለበለጠ መረጃ አድራሻ፡- በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት

ከብሩክ ህንፃ ፊት ለፊት ቴሌ አጠገብ ከተሰራው አዲሱ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ህንፃ ውስጥ 1ኛ ፎቅ ወደ ቀኝ ሲታጠፉ የወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት በአካል

በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0113301548/0911921780/ ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።

 

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender