Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462128588
  • Website
  • Deadline15 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-15 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing , Furniture

መ/ቤታችን በሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ፈርኒቸር ዕቃዎችን ብቁ ተጫራችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)


የመጀመሪያ ዙር የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር፡-ሲ/መ/ባ/001/2018

ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የፈርኒቸር ዕቃዎች ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

መ/ቤታችን በሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ፈርኒቸር ዕቃዎችን ብቁ ተጫራችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

 

ተ/ቁ

የዕቃው አይነት

Specification

ብዛት

1

ፈርኒቸሪ (furture)

 

 

 

በዚሁ መሠረት -

1.     ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ወይም የአገልግሎት የሥራ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የሚያሳይ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2.     ተጫራቾች ዋጋውን በታሽገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን በተለያዩ ፖስታ በማድረግ አንድ ቴክኒካል ኦርጅናል ሁለት ኮፒ እና ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያውንም በተለየ ፖስታ ለብቻው ማቅረብ ይኖርበታል ፡፡

3.     ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር -5 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተመለከተው መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡

4.     አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን እስከ 11ኛ ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡

5.     ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋ 0.5% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ከተረጋገጠ ቼክ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዶች ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልከ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡

6.     ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡

7.     ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8.     ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ ፡፡

 

ስልክ ቁጥር፣ 0462-128-446

 

ሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን

ሀዋሳ

 

Save Tender