Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢንሃንሲንግ ቻይልድ ፎከስድ አክቲቪቲስ (Enhancing child Focused Activities)
  • Address አዳማ ጎሮ ቀበሌ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0966266060
  • Website
  • Deadline16 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityየሚገዙትን እቃ ዋጋ 20%
  • opening date2026-01-17 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing

ኢንሃንሲንግ ቻይልድ ፎከስድ አክቲቪቲስ (Enhancing child Focused Activities) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ ሼልፎች፣ ጠረጴዛና ወንበሮች ሁኔታ እና ቦታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ኢንሃንሲንግ ቻይልድ ፎከስድ አክቲቪቲስ (Enhancing child Focused Activities)


 

ያገለገሉ እቃዎች የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 3/2018ዓ.ም

 

ኢንሃንሲንግ ቻይልድ ፎከስድ አክቲቪቲስ (Enhancing child Focused Activities) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ ሼልፎች፣ ጠረጴዛና ወንበሮች ሁኔታ እና ቦታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ እቃዎቹን መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ አዳማ ጎሮ ቀበሌ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች ለጨረታው የቀረቡትን የተለያዩ አይነት ያገለገሉ እቃዎች አዳማ በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት በአካል ተገኝተው በማየት ዋጋቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከላይ በተገለፀው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  2. ጨረታው በተዘጋ በማግስቱ ከረፋዱ 4፡00 ሰአት በድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል፡፡
  3. ተጫራቾች የሚገዙትን እቃ ዋጋ 20% በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ሲ.ፒ.ኦ ኢንሃንሲንግ ቻይልድ ፎከስድ አክቲቪቲስ (Enhancing child Focused Activities) ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  4. የጨረታው ማስረከቢያ ዋስትና ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሽናፊዎች የጨረታው ውጤት በፀደቀ በአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል፡፡
  5. አሸናፊዎች ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ሙሉ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ እቃዎቹን የመረከብ ግዴታ አለባቸው፣ ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ወይም ሲፒኦ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  6. ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0966266060 ወይም 0910414710

 

ኢንሃንሲንግ ቻይልድ ፎከስድ አክቲቪቲስ

 

Save Tender