Tender Detail

Tender Details

  • Company ደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ልማት ማህበር (ደኢህልማ)
  • Address ምሥራቅ ክፍለ ከተማ ዳግም ጂምናዚየም ፊት ፊት ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046 220 9608
  • Website
  • Deadline13 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security10%
  • opening date2026-01-13 00:00:00
  • Categories Vehicle

ደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ልማት ማህበር (ደኢህልማ) በኢትዮጵያ ሲቪል ማህረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ 1113/2011 መሠረት ዳግም ምዝገባ ቁጥር 1104 የተመዘገበ አካባቢ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ ያገለገለ አንድ ተሽከርካሪ (ማህንዲራ የመስክ መኪና) እና ሌሎች የቢሮ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ልማት ማህበር (ደኢህልማ)


 

ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 1104-0002-2025

 

ደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ልማት ማህበር (ደኢህልማ) በኢትዮጵያ ሲቪል ማህረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ 1113/2011 መሠረት ዳግም ምዝገባ ቁጥር 1104 የተመዘገበ አካባቢ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ ያገለገለ አንድ ተሽከርካሪ (ማህንዲራ የመስክ መኪና) እና ሌሎች የቢሮ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ከማቅረባቸው በፊት ንብረቶችን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ቀናት ልማት ማህበሩ ጽ/ቤት በአካል ቀርበው ማየት ይችላሉ፡፡
  2. በጨረታው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል፡፡
  3. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት በሚገዙበት የጨረታ መግዣ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በልማት ማኅበሩ ስም በማቅረብ ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ በጨረታ ለመሳተፍ ይችላሉ። ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከውድድሩ ቢወጡ ወይም ጨረታውን በሕግ አግባበብ ከተደነገገው ውጪ የማጭበርበር ተግባር ሲፈፅም ከተገኘ የጨረታው ማስከበሪያው ያስያዙት ገንዘብ ለልማት ማህበሩ ገቢ ይሆናል፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያው የአሸናፊዎች ዝርዝር በማስታወቂያ ሰሌዳ እንደተገለጸ በኋላ ለተጫራቾች በቀጣዩ 3 የሥራ ቀናት ተመላሽ ይደረጋል።
  5. ለጨረታ የተዘጋጀውን የንብረቶች ዝርዝር የያዘውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ተከታታይ 10 ቀናት ደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ልማት ማህበር (ደኢህልማ) ዋና ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ንብረቶች በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ደኢህልማ ዋና ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን በማስገባት በዚሁ ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ተገኙበት በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ዘግይቶ የደረሰ መወዳደሪያ ተቀባይነት የለውም።
  7. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉበትን ንብረቶች ሙሉ ክፍያ በመፈፀም በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ለዚሁ በተከፈተ አካውንት ገቢ በማድረግ ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል፤ በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለልማት ማህበሩ ገቢ ሆኖ በድጋሚ ጨረታ ላይ ይውላል፡፡
  8. መ/ቤቱ የጨረታ ሰነዱ መስተካከል አለበት ብሎ ሲያምን ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት በማንኛውም ጊዜ የጨረታ ሰነዱን ማስተካከል የሚችል ሲሆን ይህንንም ለሁሉም ተጫራቾች በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ይገለጻል።
  9. የስም ዝውውርና ተዛማጅ ወጪዎችን የጨረታው አሸናፊ ራሱ ይሸፍናል፡፡
  10. ልማት ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ለተጨማሪ መረጃ ደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ልማት ማህበር በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሀዋሳ ከተማ

 

ምሥራቅ ክፍለ ከተማ ዳግም ጂምናዚየም ፊት ፊት /ስልክ ቁጥር 046 220 9608/ 0943956089/0973621368

ፖ. ሣ. ቁ. 812 ማግኘት ይችላሉ።

 

ደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ልማት ማህበር (ደኢህልማ)

 

Save Tender