የደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ በወረዳው ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤት ተሽከርካሪዎች የሚውል የጎማ ግዥ ከአቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ በወረዳው ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤት ተሽከርካሪዎች የሚውል የጎማ ግዥ ከአቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል።
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው።
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል /የምትችል።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ/ለች እና ክሊራንስ ከግብር መ/ቤት ያቀረበ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል /የምትቸል።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆን እና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል/ የምትችል ፣
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዶች ጋር የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በአሃዝ እና በፊደል መግለጽ አለባቸው: በፊደል እና በአሃዝ መካከል ልዩነት ካለው በፊደል የተገለጸው ይወሰዳል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ሁለት መቶ (200) በመክፈል ከደ/ቤ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10/አስር/ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል አንድ (1) ኦርጅናል እና አንድ (1) ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል አንድ (1) ኦርጅናል እና አንድ (1) ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ማቅርብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል: ያለበለዚያ ያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሰነድ ሳይ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ፖስታውን በደ/ቤ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15(አስራ አምስት) የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከሰዓቱ 9፡00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከቀኑ 9:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፣፣
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
አድራሻ - የደ/ቤ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ደብረወርቅ
ደ/ወርቅ ስልክ፡-09 66 88 69 73 / 09 10 99 77 47 / 09 29 24 17 31 በመደወል መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።
የደቡብ ቤንች/ወ/ፋ/ጽ/ቤት
