Tender Detail

Tender Details

  • Company Water Works Construction Enterprise (WWCE) (የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
  • Address ባህርዳር ከተማ በዳግማዊ ምኒልክ ክ/ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት፣ በኮምቦልቻ በሚገኘው ቢሯችን እንዲሁም በአዲስ አበባ ሳሪስ ዳማ ሆቴል በሚገኘው ቢሯችን ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-67-44-22-04
  • Websitehttps://wwc.com.et/
  • Deadline23 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid Securityየተጨማሪ እሴት ታክስን 15% ጨምሮ የሚገዙበትን ዋጋ 10% /አስር በመቶ/
  • opening date2026-01-23 00:00:00
  • Categories Machinery , Vehicle

የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር በሚገኘው ቢሯችን እና ኮምቦልቻ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የሚገኙትን ያገለገሉ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Water Works Construction Enterprise (WWCE) (የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን)


 

ለ2ተኛ ጊዜ የወጣ ያገለገሉ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ሽያጭ

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ግ/ጨ/ቁጥር 46/2018

 

የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር በሚገኘው ቢሯችን እና ኮምቦልቻ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የሚገኙትን ያገለገሉ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች የሚሸጡትን ያገለገሉ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ዋናው መ/ቤት ፕላስቲክ ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው ስቶር፣ ኮምቦልቻ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በሚገኘው በአካል በመገኘት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በሥራ ሰዓት በመመልከት ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይቻላል፡፡
  2. በጨረታው ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆነ ድርጅት ወይም ግለሰብ ሁሉ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በማህበር ለመወዳደር የሚፈልግ የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ በፍትህ ተቋም የተሰጠውን ሕጋዊ ውከልና ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ባህርዳር ከተማ በዳግማዊ ምኒልክ ክ/ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሯችን ቢሮ ቁጥር 02 ፣ ኮምቦልቻ በሚገኘው ቢሯችን እንዲሁም አዲስ አበባ ሳሪስ ዳማ ሆቴል አካባቢ በሚገኘው ቢሯችን ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /bid bond/ የተጨማሪ እሴት ታክስን 15% ጨምሮ የሚገዙበትን ዋጋ 10% /አስር በመቶ/ በባንክ ማስያዥያ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ቼክ እንደ ማስያዥያ ማቅረብ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ባህርዳር ከተማ በዳግማዊ ምኒልክ ክ/ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት፣ በኮምቦልቻ በሚገኘው ቢሯችን እንዲሁም በአዲስ አበባ ሳሪስ ዳማ ሆቴል በሚገኘው ቢሯችን በዙም በተመመሳይ ሰዓት የሚከፈት ሆኖ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መከፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
  6. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ሙሉ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙትን የጨረታ ማስያዣ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይሆናል፡፡
  7. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በከፈሉ ማግስት ጀምሮ እቃውን በ15 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግን በተባለው ቀን የማያነሱ ከሆነ ያስያዙት ሲፒኦ ተወርሶ ኮርፖሬሽኑ የሚያዋጣው ከሆነ 2ኛ ለወጣው ተጫራች የሚሸጠው ይሆናል፡፡
  8. ጨረታ ሰነዱን ባህርዳር ከተማ በዳግማዊ ምኒልክ ክ/ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሯችን ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር ብቻ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ለውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የባንከ ሂሳብ ቁጥር 1000265163223 አስገብተው ማስረጃ በማቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. ገዥው በተፈቀደለት የጊዜ ገደብ ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ እቃውን መረከብ ባይችል ያጋጠመውን ችግር ከበቂ ማስረጃ ጋር በጽሑፍ አመልከቶ የድርጅቱ የሚመለከተው ኃላፊ ሲፈቅድ ብቻ የርክክብ ጊዜው ሊራዘም ይችላል፡፡
  10. የሚሸጡት ያገለገሉ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችንና ማሽነሪዎችን በተመለከተ የሚኖር ማንኛውንም ወጪ በአሽናፊው የሚሸፈን በመሆኑ በዚህ አግባብ ግዴታ የሚገባ ይሆናል።
  11. ለእያንዳንዱ እቃ ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተወዳዳሪ አሸናፊ ሆኖ ይመረጣል፡፡
  12. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም፡፡ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ - በስልከ ቁጥራችን 09-67-44-22-04 እና 09-85-07-75-18 እንዲሁም በኮርፖሬሽናችን ዌብሳይት www.wwc.com.et እና https://www.facebook.com እንዲሁም ቴሌግራም https://t.me/WaterWorks Corporation Official መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

 

Save Tender