የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች (Furniture) ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢአጽ/ግንአዳ/010/2018
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች (Furniture) ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
- በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ከድረ-ገጹ (Website) እትመው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ፣ የግብር መለያ ሰርተፍኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቶች የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቶች ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ለዘጠና ቀናት የሚቆይ ቅድመ ሁኔታ ያላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች መወዳደሪያ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጥር 6 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ማለትም ጥር 6 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት በኢንተርፕራይዝ አገልግሎት ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 011-5512400 የውስጥ መስመር 237/262 እንዲሁም በቀጥታ 011-5504931 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት
