በአ/ብ/ከ/መ ጤና ጥበቃ ቢሮ በሰ/ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ የሸዋሮቢት ጤና አጠበባቅ ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉ ሎትı የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች ሎት2 የተለያዩ የጽዳት እቃዎች ሎት3. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ አከሰሰሪዎች ሎት4.የተለያዩ የደንብ ልብሶች ብትን ጨርቆች ሎት5 የተዘጋጁ የደንብ ልብሶች እና ጫማ ሎት6.የተለያዩ ህትመቶች ሎት 7 አንሶላ ሎት8. የተለያዩ ፈርኒቸሮች ሎት9, የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ እንዲገዛ ይፈልጋል፡፡
የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጤና አጠባበቅ ጣቢያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአ/ብ/ከ/መ ጤና ጥበቃ ቢሮ በሰ/ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ የሸዋሮቢት ጤና አጠበባቅ ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉ ሎትı የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች ሎት2 የተለያዩ የጽዳት እቃዎች ሎት3. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ አከሰሰሪዎች ሎት4.የተለያዩ የደንብ ልብሶች ብትን ጨርቆች ሎት5 የተዘጋጁ የደንብ ልብሶች እና ጫማ ሎት6.የተለያዩ ህትመቶች ሎት 7 አንሶላ ሎት8. የተለያዩ ፈርኒቸሮች ሎት9, የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ እንዲገዛ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
1. የዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቀድ ያላቸው እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን /TIN/ ያላቸው
3. የዕቃው መጠን ብር 200,000 ብር በላይ ከሆነ የቫት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋርአያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የእቃው አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ በጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 28 ማግኘት ይችላሉ
7. ተጫራቾቹ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጨረታ ጠቅላላዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በግዥ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 36 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በአዲስ አበባ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው እለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
10. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ተጫራቾች ናሙናውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት አለባቸው፡፡
11. የጨረታ መከፈቻውንና መዝጊያው ከመንግስት ስራ ቀን ውጪ ወይም በበዓል ቀን ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይዘጋል ይከፈታል።
12. ተወዳዳሪ ድርጅቱ ያሸነፉበትን እቃዎች በሸዋሮቢት ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ንብረት ከፍል ድረስ የማቅረብና የማስረከብ ኃላፊነት አለባቸው፡፡
13. ውድድሩ በጥቅል /በሎት ስለሆነ ተጫራጮች በከፊል መሙላት አይችሉም፡፡
14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊልም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15.በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 36 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-664-0075 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ጨረታውን ስትሞሉ በጥቅል ዋጋ መሆኑን አውቃችሁ እንድትሞሉ፡፡
የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጤና አጠባበቅ ጣቢያ
