በደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የጂንካ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለ2018 በጀት አመት ለሳይትና ለቢሮ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ተሽከርካሪዎች ኪራይ አገልግሎት ግዥ ለሁለተኛ ዙር፣ የንጽህና መጠበቂያ እቃዎች እና የግንባታ እቃዎች የመጀመሪያ ዙር በወጣ ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመከራየት እና ለመግዛት ይፈልጋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የጂንካ ዲስትሪክት ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የጂንካ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለ2018 በጀት አመት ለሳይትና ለቢሮ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ተሽከርካሪዎች ኪራይ አገልግሎት ግዥ ለሁለተኛ ዙር፣ የንጽህና መጠበቂያ እቃዎች እና የግንባታ እቃዎች የመጀመሪያ ዙር በወጣ ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመከራየት እና ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት በጨረታው ስመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው መስፈርት፦
- በጨረታው ለመሳተፍ በመስኩ የንግድ ፍቃድ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ፣የምስክር ወረቀት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ፣
- ዋጋ የሚያቀርቡበትን የጨረታ ሰነድ ፋይናንሻሉን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ በማድረግ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና አድራሻቸውን በትክክል ማስፈር ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ተሽከርካሪዎች ውስጥ ቢያንስ በቁጥር አንድ የኪራይ ተሽከርካሪ የግል ንብረት መሆኑን ሊብሬ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች በራስ ትራንስፖርት ጂንካ ዲስትሪክት ግቢ መጋዝን ድረስ በማጓጓዝ የሚያስረክቡ ይሆናል፤
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የግንባታ ዕቃዎች ማለትም ፌሮ ብረት 50 ሣንቲ ሜትር ቁርጥራጭ ብረት እና የንጽህና መጠበቂያ እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ከዚህ ቀደም መ/ቤቱ ባወጣቸው የአገልግሎት ሆነ የእቃ ግዥ ጨረታዎች የጨረታ ሂደት ላይ እና ከጨረታ በኋላ የመንግስትን ስራ ያላስተጓጎሉ እና ከማንኛውም አይነት የዲስፕሊን ክስ እና ቅጣት ነጻ የሆኑ መሆን ይጠበቅባቸዋል፣
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆነባቸውን ተሽከርካሪዎች ወጪ በራስ ይሸፍኑና ድርጅቱን የሚጠይቁ ይሆናል፣
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም።
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክር ተጫራች ከጨረታው የሚሰረዝ ሆኖ ለወደፊቱም መ/ቤቱ በሚያወጣቸው የአገልግሎት እና እቃ የግዥ ጨረታዎች ላይ እንዳይሳተፍ ይደረጋል።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ጂንካ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ፋይናንስና ሎጂስቲክስ ቢሮ ቁጥር 01 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ 100 ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፣
- የጨረታ ጊዜው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ (15) አስራ አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ፀንቶ ይቆያል፣
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ (15) አስራ አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ይቆይና በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን ከቀኑ 9፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሣጥኑ ይታሸግና በ9፡30 ይከፈታል፣
- ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ30 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፣
- የእቃ ግዥ ተጫራቾች ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ /ቫትን ጨምሮ/ የጨረታ ማስከበሪያ 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ እና የአገልግሎት ግዥ ተጫራቾች 10,000 አሥር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ከሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው የቀረቡ የአገልግሎት ግዥ ሆነ የዕቃ ቁጥሩን እንደአስፈላጊነቱ መ/ቤቱ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
ለበለጠ መረጃ 0467751879/0916853591 /0930755002
በደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የጂንካ ዲስትሪክት ጽ/ቤት
