Tender Detail

Tender Details

  • Company የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር ግብርና ገጠር ልማት መምሪያ
  • Address , Phone: 0918730673
  • Website
  • Deadline13 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security2%
  • opening date2026-01-13 00:00:00
  • Categories Transportation Service And Cargo

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ የሰሜን ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ለ2018/2019 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል 88,477 ኩ/ል የአፈር ማዳበሪያ በዞናችን ካለው ደባርቅ ዩኒየን በስሩ ባሉ 33 መሠረታዊ ማኅበራት መጋዘን ድረስ ለማጓጓዝ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ውል ከተፈፀመበት ቀን እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ባለው 7 ወር ጊዜ የሚቆይ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር ግብርና ገጠር ልማት መምሪያ


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ የሰሜን ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ለ2018/2019 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል 88,477 ኩ/ል የአፈር ማዳበሪያ በዞናችን ካለው ደባርቅ ዩኒየን በስሩ ባሉ 33 መሠረታዊ ማኅበራት መጋዘን ድረስ ለማጓጓዝ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ውል ከተፈፀመበት ቀን እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ባለው 7 ወር ጊዜ የሚቆይ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች

  1. የንግድ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር /ቢሮ/ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድና የዘመኑን የመንግሥት ግብር ስለመከፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
  2. የገቢዎች ጉምሩክ ባለሥልጣን ግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት /ቲን/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. በጨረታው የሚሣተፉ ተጫራቾች ከ70 ኩ/ል በላይ የሚጭኑ ተሽከሪካሪዎች የሚያቀርቡ ከሆነ ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. እንዲሁም ተጫራቾች የሚያቀርቡት ከ70 ኩ/ል በታች ከሆነ በክልል ትራንስፖርት ቢሮ ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።
  5. የተሽከርካሪ ዝርዝር ተ.ቁ የሰሌዳ ቁጥር የመኪናው ዓይነትና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ወይም ከክልል መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የተሰጠ የ2017/18 ዓ.ም ወቅታዊ የታደሰ ምዝገባ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሜችሉና በጨረታዉ አሽናፊ ከሆነ በኋላ ለሁለተኛ ወገን ማስተላለፍ አይችልም፤
  6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1 እስከ 5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
  7. የሚጓጓዘውን የአፈር ማዳበሪያ አይነት፣ መጠን ርቀት በኪሎሜትር ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 01 ማግኘት ይቻላል፤
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ. ኦ/ ወይም በሁኔታዎች ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በደባርቅ ዩኒየን ስም ማስያዝ አለባቸው።
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን በአንድ ፖስታ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በማሸግ በሰሜን ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ቢሮ ቁጥር 204 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ20/04/2018 እስከ 04/05/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይውላል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰሜን ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ በቀን 05/05/2018 ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  11. አንድ ተጫራች በዩኒየኑ ውስጥ ከተዘረዘሩት ማኅበራት መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይችልም ከውድድር ውጭ ያደርጋል።
  12. መስሪያ ቤቱ የሚያወዳድረው ለሁሉም መሠረታዊ ማኅበር በሚያቀርበው ጥቅል ዋጋ/ሎት ነው።
  13. መምሪያው አማራጭ ካገኘ መሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 203 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 73 06 73 / 09 84 17-11 27 በመደወል ማግኘት ይቻላል።

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር ግብርና ገጠር ልማት መምሪያ

Save Tender