በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2018 ዓ.ም ከካፒታል በጀት እና ከመደበኛ በጀት ሞተር ብስክሌት፣ የመኪና ጎማ፣ የሞተር ጎማ እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2018 ዓ.ም ከካፒታል በጀት እና ከመደበኛ በጀት ሞተር ብስክሌት፣ የመኪና ጎማ፣ የሞተር ጎማ እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች
- በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
- ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ዝርዝር የጨረታ ሠነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የግዥ ከፍያ ንብረት አስ/ርደጋፊ የሥራ ሂደት እየመጡ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሠነድ መግዛት ይኖርባቸዋል።
- 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ የተረጋገጠ CPO ከሠነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። CPO በባንከ ሠራተኞች ፊርማ የተረጋገጠ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን የዋጋ ማቅረቢያ ሠነዶቻቸውን ኦርጅናሉን በፖስታ በማሸግ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ መጨረሻው ቀን ከቀኑ 10፡00 ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ የጨረታ ሠነዶቻቸውን ማስገባት አለባቸው። ጥራቱን በጥንቃቄ እናያለን።
- ዝርዝር የጨረታ ሠነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አሥራ አምስት ቀናት/ ከቀኑ 10፡00 ድረስ በሣጥኑ መጨመር አለባቸው። በዕለቱ 11፡00 ታሽጎ በሚቀጥለው ቀን ማለትም በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡30 ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። በሠነዱ ከተባለው ውጪ ማቅረብ አይቻልም።
- በጨረታው ሠነድ የተፃፈውን የዕቃ ዓይነት ተጫራቾች በትክክል መሙላት አለባቸው። የሚያቀርቧቸው ዋጋ ከቫት ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ያሸነፈ ተጫራች ዕቃውን እስከ መ/ቤቱ ድረስ ያቀርባል። ፍርድ ቤቱ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን መለወጥ ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ በስልክ ቁጥር 0465512100 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
