የመ/ሜዳ ከተማ መሠረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከ"ሀ" እስከ "ሠ" በተዘረዘረው መሰረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች እና የግንባታ ደረጃዎች የተዘጋጀ ቦታን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
የመ/ሜዳ ከተማ መሠረት ልማት ጽ/ቤት
የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን
የመ/ሜዳ ከተማ መሠረተ ልማት ጽ/ቤት
የጨረታ ዙር 21ኛ
የጨረታው ዓይነት /መደበኛ ጨረታ/
- የመ/ሜዳ ከተማ መሠረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከ"ሀ" እስከ "ሠ" በተዘረዘረው መሰረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች እና የግንባታ ደረጃዎች የተዘጋጀ ቦታን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በመ/ሜዳ ከተማ መሠረት ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 001 ዘወትር በስራ ሰዓት መግባት የሚቻል መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ብቻ ይሆናል።
- ጨረታው የሚዘጋው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተቆጥሮ በ11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይሆናል።
- ቦታውን መጎብኝት ለሚፈልግ ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሀ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተቆጥሮ 11ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ላይ 5፡00 ሰዓት ላይ በመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ሁለገብ አዳራሽ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ አለባቸው።
- በጨረታው ለመሣተፍ የምትፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ መ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 001 በአካል በመገኘት መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 685 11 04 መጠየቅ ይችላሉ፤
የመ/ሜዳ ከተማ መሠረት ልማት ጽ/ቤት
