Tender Detail

Tender Details

  • Company Wolaitta Development Association (የወላይታ ልማት ማህበር)
  • Address አ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሰሜን ሆቴል ፊት ለፊት ዳትስን ሰፈር ወደ ግራ በሚያስገባው አስፋልት 100 ሜትር ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0461801191
  • Websitehttps://wolaittada.org.et/
  • Deadline20 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • Bid Securityለመወዳደር ባቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ በማስላት 2%
  • opening date2026-01-20 00:00:00
  • Categories Printing And Publishing

ወላይታ ልማት ማህበር የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ለማሳተም የሕትመት አገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ አሸናፊውን በውል ለማሳተም ይፈልጋል።

Wolaitta Development Association (የወላይታ ልማት ማህበር)


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ወልማ 06/2025

 

ወላይታ ልማት ማህበር የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ለማሳተም የሕትመት አገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ አሸናፊውን በውል ለማሳተም ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች አሟልተው መቅረብ ያለባቸው መስፈርቶችና ግዴታዎች፤

  1. በግዥና ንብ/አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ ሰርፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ም/ም/ወረቀት፤ ሕጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ እና ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 9/ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ዘወትር በማህበሩ ሥራ ቀንና ሰዓት በወላይታ ልማት ማህበር አ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሰሜን ሆቴል ፊት ለፊት ዳትስን ሰፈር ወደ ግራ በሚያስገባው አስፋልት 100 ሜትር ገባ ብሎ ከሚገኘው ቢሮ እና በወላይታ ሶዶ ወላይታ ልማት ማህበር ዋ/ና ጽ/ቤት ከሚገኘው ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 13 ሰነዱን ገዝተው መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ለተሸናፊዎች ከጨረታ ግምገማ በኋላ የሚመለስ የጨረታ ዋስትና ለመወዳደር ባቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ በማስላት 2% በባንክ የተመሰከረበት በወላይታ ልማት ማህበር ስም የተሰራውን ሲፒኦ ከጨረታ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር አያይዘው በታሽገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የውል ማስከበሪያ ዋስትና አሸናፊነቱ ከተረጋገጠበት/ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሎት ከአምስት እስከ አሥር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ባሸነፉበት ዋጋ መጠን ተሰልቶ 10% በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሠከረ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት። ለማስያዝ ፈቃደኛ ካልሆነ ለጨረታ ዋስትና ያስያዘው ብር ሙሉ በሙሉ ለማህበሩ ውርስ ይደረጋል።
  6. አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብና አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ አገልግሎቱን አላቀርብም ማለት የጨረታ ዋስትናውን ያስቀጣል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ ማቅረቢያ ፖስታቸውን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማድረግ የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በወላይታ ልማት ማህበር ግዥና ንብረት አስ/ር ክፍል ቢሮ ቁጥር 13 ውስጥ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 15ኛው የሥራ ቀን 10 /አስር ሰዓት/ ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. የጨረታ ሳጥን የሚከፈተው በ15ኛው የሥራ ቀን እስከ 9፡30 ሰዓት ድረስ የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ገቢ ሆኖ በ10፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት በእለቱ በ10፡30 ሰዓት በወላይታ ሶዶ በሚገኘው ወላይታ ልማት ማህበር ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 13 ይከፈታል። 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓትና ቦታ ጨረታው ይከፈታል።
  9. ጨረታ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ካለው ወይም ግልጽ ሆኖ ካልታየ ተቀባይነት አኖረውም።

 

ማሳሰቢያ፡- ማህበሩ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0461801191/01111572842 መጠቀም ይችላሉ።

 

የወላይታ ልማት ማህበር

 

Save Tender