Tender Detail

Tender Details

  • Company ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  • Address መካኒሳ አቦ ቤተክርስቲያን አጠገብ ኩዊንስ ህንጻ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 14 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 11 23 84 29
  • Website
  • Deadline13 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security20%
  • opening date2026-01-13 00:00:00
  • Categories Vehicle

ሚድሮክ ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር ለተለያዩ አገልግሎቶች ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር


ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ

ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር

Disposal MID 01/2018

ሚድሮክ ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር ለተለያዩ አገልግሎቶች ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት-

1.በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ከዚህ ጨረታ ጋር በተያያዘ ማንኛውም ገቢ የሚደረግ ገንዘብ በተጫራች ድርጅት ስም መሆን አለበት፡፡

2. ተጫራቾች አዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በበር ቁጥር 07 በአካል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በሚድሮክ ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር ስም በዳሸን ባንከ ጊዮን ቅርንጫፍ የሂሳብ ቁጥር 0001001000021 በማስገባት ያስገበበትን ዋናውን ደረሰኝ በመያዝ የጨረታ ሠነዱን በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው የሥራ ቀን እና ሰዓት መሰረት መውሰድ ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች አዲስ አበባ ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ ቅጥር ግቢ ውስጥ በበር ቁጥር 07 በኩል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከታኅሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት የሥራ ቀናት ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ሳይጨምር ዘወትር በሥራ ሰዓት (ጠዋት 2፡30 እስከ 6፡30 ከሰዓት በኋላ 7፡30 እስከ 11፡00) ተሽከርካሪዎቹን ማየት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታው ለሚሳተፉባቸው ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ለጨረታ ያቀረበበትን 20% የጨረታ ማስከበሪያ በሚድሮክ ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር ስም ማስያዝ ይኖርበቸዋል፡፡

5. ተጫራቾች ድርጅቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ የተሽከርካሪ ዓይነትና የሠሌዳ ቁጥር ትይዩ የሚገዙበትን ዋጋ በመጥቀስ ከጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ጋር በማካተት ጥር 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡30 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ ለመረጡት ተሽከርካሪ የዋጋ ማቅረቢያ እና CPO በታሸገ ኢንቨሎፕ በማዘጋጀት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ፡፡ ጨረታው ጥር5 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡30 ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጠዋት 4፡45 ይከፈታል፡፡

6. ሻጭ ሚድሮክ ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር ማንኛውንም የመንግሥት ዕዳ ከፍሎ ተሽከርካሪዎቹን ለመሸጥ የሚያስፈልግ ከሊራንስ በራሱ ወጪ ከሚመለከተው የመንግሥት መ/ቤት ያቀርባል፡፡

7. የጨረታ አሸናፊዎች ለሚገዟቸው ተሽከርካሪዎች የስም ማዛወሪያ እና በመንገድ ትራንስፖርት ግምትና የሽያጭ ውል ልዩነት ካለ ለሀገር ውስጥ ገቢዎች ሚኒስቴር የሚከፈል ወጪ በጨረታ አሸናፊዎች ይሸፈናል፡፡

8. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ግለሰብ /ድርጅት አሸናፊነቱ በተግለጸለት በ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን ተሸከርካሪ ሙሉ ዋጋ ገቢ በማድረግና የሺያጭ ውል በመዋዋል በርክክብ ቅፅ ተሽከርካሪውን ማንሳት ሲኖርበት ተሽከርካሪውን ማንሳት ካልቻለ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው CPO የማይመለስ ይሆናል ፡፡

9, በጨረታው የተሸነፈ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ CPO ለተጫራች ሚድሮክ ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር በሚያወጣው ፕሮግራም መሰረት እንዲመለስ ይደረጋል፡፡

ሚድሮክ ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ሕጋዊ መበት አለው፡፡

አድራሻ

አዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍስ ከተማ ናኒ ሕንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 507- ጊዮን ሆቴል አጠገብ

ማሳሳቢያ፤

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር: - +251-115-54-99-69:

ተጫራቾች ሙስ አድራሻ እና አማራጭ ስልኮቻቸውን መጥቀስ ይኖርባቸዋል፡፡

ሚድሮክ ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር

Save Tender