በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የፅህፈት መሣሪያዎች እና ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ፡-
- ሎት 1 የፅህፈት መሣሪያዎች
- ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN Number) ያላቸው፣
- የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሰውን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ዓይነት፣ አምራቹን ስም፣ የተመረተበትን ዓ.ም በዝርዝር ከዋናው ጨረታ ሰነድ መያያዝ አለበት፣
- ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ሲጠየቅ ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለፅህፈት መሣሪያዎች ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ እና ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 50,000 በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም Bid bond/ቢድቦንድ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ስም ተዘጋጅቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሎት 1 እና ለሎት 2 ከተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትን የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 100 /አንድ መቶ/ ብር በመክፈል ሰነዱን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት 2ኛ ፎቅ በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ዕቃውን ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ወልቂጤ ከተማ ድረስ ለማቅረብ የሚያስችል ዋጋ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ ታሽጎ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 2ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሣጥኑ ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ አዳራሽ በይፋ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኛ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአከል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር +251113658288 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የምታቀርቡ 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የመ/ቤቱ አድራሻ-
የወልቂጤ መብራት ሀይል አገልግሎት ፊት ለፊት ፈድሉ ህንፃ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ
ወልቂጤ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ
