Tender Detail

Tender Details

  • Company የመርካቶ ሸማ ተራ የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር
  • Address , Phone: 251911259237
  • Website
  • Deadline09 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1500.00
  • Bid Security150,000.00 /መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/
  • opening date2026-01-09 00:00:00
  • Categories Building Construction , Construction Works

በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ-01 ልዩ ስሙ መርካቶ አካባቢ የሚገኘው የመርካቶ ሸማ ተራ የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር የተጨማሪ ወለል ግንባታ ሥራ ጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ሥራ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

የመርካቶ ሸማ ተራ የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር


 

የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ-01 ልዩ ስሙ መርካቶ አካባቢ የሚገኘው የመርካቶ ሸማ ተራ የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር የተጨማሪ ወለል ግንባታ ሥራ ጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ሥራ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የተሟላ የሰው ኃይል እና ማሽነሪዎች በማቅረብ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ሥራውን ማጠናቀቅ የሚችል እና የሚከተሉትን መስፈርቶች በሟሟላት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

 

ተ.ቁ

የፕሮጀክት ስም

የሚገኝበት ቦታ

የጨረታ ዋስትና ብር መጠን

የተቋራጭ ደረጃ

ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ

1

ለመርካቶ ሸማ ተራ የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር የተጨማሪ ወለል ግንባታ ሥራ

አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 መርካቶ

150,000.00

GC-6/BC-5 እና ከዚያ በላይ

60 ቀናት

 

  1. የ2017/18 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ከፌደራል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን እንዲሁም በ2017 በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው (Supplier List)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታው ውድድር ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካል አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ፤ ፋይናንሻል አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ በማሸግ በድምሩ 4 (አራት) ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ፊርማ፣ ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የፐሮጀክት ስም በመጻፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም (BID BOND or BID SECURITY) ለብቻ በታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባችዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ለ 60+28 ቀናት የሚያገለግል ወይም የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND or BID SECURITY) በባንክ ትእዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /UNCONDITIONAL BANK GUARANTEE በመርካቶ ሸማ ተራ የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር ስም የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 (ሰባት) የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡30 ድረስ አዲስ ክተማ ከፍለ ከተማ ወረዳ 01 መርካቶ ሸማ ተራ የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር ሕንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ በአክሲዮን ማሀበሩ ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ብር 1,500.00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) በአክሲዮን ማህበሩ የባንክ ሂሳብ ገቢ አድርጋችሁ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ጥር 1 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችዋል፡፡ ጨረታው በዚያው ቀን ጥር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  5. አከሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ መርካቶ ሸማ ተራ የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር ሕንፃ 4ኛ ፎቅ ለአክሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት በጽሁፍ ወይም በአካል በመቅረብ ወይም

በስልክ ቁጥሮች፡- 251-0112-73-39-90/+251-911-65-79-66

+251-911-22-60-45/+251-911-25-92-37 ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ።

አድራሻ፡- መርካቶ ሸማ ተራ የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር ሕንፃ 4ኛ ፎቅ አከሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት መርካቶ አዲስ ከተማ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ጀርባ

 

የመርካቶ ሸማ ተራ የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር

 

Save Tender