Tender Detail

Tender Details


በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በሜካናይዝድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለሥራ አገልግሎት ላይ የሚውል ከዚህ በታች የተገለፀውን የግዥ ፍላጎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በሜካናይዝድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በሜካናይዝድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለሥራ አገልግሎት ላይ የሚውል ከዚህ በታች የተገለፀውን የግዥ ፍላጎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. የተለያዩ የቀላል ጥገና የኮንስትራከሽን እቃዎች፣ የኤሌክትሪክ የቯንቯ እና ሊፍት ፓምፕ (Electrical surface pump) እቃዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ የሆነ ነጋዴ ተጫራች በጨረታው መወዳደር ይችላል።
  2. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የጨረታ ዘርፍ በሚፈቅደው ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ; የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት፣ የቫት የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢነት መታወቂያ ሰርተፍኬት እና ካለፉት 3ወር የቫት ሪፖርት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች ይወዳደራሉ፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ከታወቁ የፋይናንስ ተቋሞች በተመሰከረላት ባንክ ሲ.ፒ.ኦ እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የሚመረቱበትን የዋጋ ማቅረቢያው ላይ በግልፅ ያለምንም ስርዝ ድልዝ በመፃፍ አርጅናል እና ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. የጨረታ ሰነዱን ከተጫራቾች ዝርዝር መመሪያ ጋር የማይመለስ 300.00 ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ከሰአት በኋላ 8፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ በር 200 ሜትር ዝቅ ብሎ ከሚገኘው የሜ/ድ ዕዝ ጠ/መምሪያ ግዥ ቡድን ቢሮ አንደኛ ፎቅ ቁጥር 101 ሰነድ መግዛት ይቻላል፡፡
  • መስሪያቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ጨረታው ጥር 1/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ ከረፋዱ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሜ/ድ ዕዝ ግዥ ቡድን በሚያዘጋጀው ቦታ ይከፈታል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0911043690

ወይም 0911025079 ይደውሉ።

 

የሜካናይዝድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ

 

Save Tender