የባቲ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ መሬት ልማት ቡድን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት 8 (ስምንት) ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት የሚውል ቦታ እና 6 (ስድስት) ለድርጅት/ንግድ የሚውል ቦታ በድምሩ 14 (አስራ አራት) ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል።
የባቲ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
የ2018 የ1ኛ ዙር መደበኛ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
- የባቲ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ መሬት ልማት ቡድን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት 8 (ስምንት) ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት የሚውል ቦታ እና 6 (ስድስት) ለድርጅት/ንግድ የሚውል ቦታ በድምሩ 14 (አስራ አራት) ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል።
በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ20/4/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል በባቲ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የባቲ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ አዳራሽ ጎን UIIDP ቢሮ በሥራ ሰዓትበአካል በመቅረብ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከ 20/04/2018ዓ.ም እስከ 04/05/2018ዓ.ም እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ይሆናል።
- ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልግ ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሐ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል።
- ጨረታው የሚዘጋው 4/5/2018ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈተው በ5/5/208 ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት በባቲ ከተማ ማዘጋጃ አዳራሽ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል።
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወይም በባቲ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተልማት ጽ/ቤት የባቲ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ አዳራሽ ጎን UIIDP ቢሮ በሥራ ሰዓት በአካል በመቅረብ ማግኘት ይቻላል።
ማሳሰቢያ፡- መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የባቲ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
