ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
Berhanena selam printing enterprise (ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 010/18
ድርጅታችን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፦
በጨረታ አንድ (ሎት 1) Kyocera Tasklfa 4004i/5004i/6004i/7004i/ Toner ብዛት 100 ግዥ፤
በጨረታ ሁለት (ሎት 2)፡- የሃይሩፍ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት ግዥ፤ ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲስ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 300.00 ከፍለው በመግዛት ፋይናንሺያል የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው።
ጨረታው 19/5/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰአት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅደመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
ስልክ ቁጥር 011-1-55-52-30
ድረ ገፅ (www.ethbspe.org)
Berhanena selam printing enterprise
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት
