በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት በግናብ ቀበሌ ከገብጥ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እስከ ግናብ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት አዲስ የጠጠር መንገድ ግንባታ እና ከሐዋሪያት እስከ የገብጥ ሚካኤል ነባር የጠጠር መንገድ ለመጠገን ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋሉ።
በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር-0001
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት በግናብ ቀበሌ ከገብጥ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እስከ ግናብ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት አዲስ የጠጠር መንገድ ግንባታ እና ከሐዋሪያት እስከ የገብጥ ሚካኤል ነባር የጠጠር መንገድ ለመጠገን ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋሉ። በመሆኑም፡-
- GC/RC ደረጃ 9ኝና ከዛ በላይ የታደሰ የግንባታ ፍቃድ ያላችሁ፤
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የተ.እታ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ የምስከር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለምሁርና አክሊል ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ከምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ/ፅ/ቤት ግዢ ቢሮ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 (ሃያ) ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 5፡00 ድረስ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴከኒካል እና ፋይናንሽያል ዶክመንት ሲያቀርቡ፡-
ሀ. ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ቅጂ ሰነዶችን በታሸገ ፖስታ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ) በምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከኦሪጅናል ዶክመንት ጋር በማድረግ እና ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግ ቴክኒካል በሚል በመለየት፤
ለ. ፋይናንሽያል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ቅጂ ሰነዶችን በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግ ፋይናንሽያል በሚል በመለየት እስከ 20ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ አላማ በተዘጋጀው የመጫረቻ ሰነድ ማቆያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ይታሸጋል።
- የጨረታው ቴከኒካል ዶክመንት በሃያኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታው እንዳይከፈት አያደርግም።
- የፋይናንሽያል (የፕሮጀክቱ የግንባታ ዋጋ) ከቴክኒካል ግምገማ ውጤት በኋላ የቴክኒክ ግምገማውን ያለፉ ተጫራቾች ሰነድ ብቻ ጽ/ቤቱ በማስታወቂያ በሚገልጸው ቀን ይከፈታል።
- የቫት ገንዘብ ክፍያ የምንፈጽመው የጠቅላላው የቫት ገንዘቡ 50% ብቻ ሲሆን ቀሪው 50% ደረሰኝ ቆርጠን በመስጠት እራሳችን የምንሰበስብ መሆኑን እንገልጻለን።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይተላለፋል።
- ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ:- 0113430173/0113430614 ይደውሉ
በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
