የጅማ ገበሬዎች ሁለገብ የህብረት ሥራ ዩኒዬን ለ 2018/19 የምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያ በዞኑ ውሰጥ ከሚገኙ ማዕከላዊ መጋዘኖች ለማህበራት ለማጓጓዝ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉትን የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የጭነት አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጅማ ገበሬዎች ሁለገብ የህብረት ሥራ ዩኒዬን
ለ2018/19 የምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያ
ለማጓጓዝ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጅማ ገበሬዎች ሁለገብ የሀብረት ሥራ ዩኒዬን ለ 2018/19 የምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያ በዞኑ ውሰጥ ከሚገኙ ማዕከላዊ መጋዘኖች ለማህበራት ለማጓጓዝ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉትን የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የጭነት አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሚጓጓዘው የአፈር ማዳበሪያ አይነትና ብዛትም የሚከተለው ይሆናል፡፡
- ዳፕ (DAP) 361,248 ±25% ኩንታል፤
- ዩሪያ (UREA 253,881 +25% ኩንታል፤
- በድምሩ 615,129 +25% ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ
በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የዘመኑ የታደሰ ሀጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤
- በአቅራቢነት የተመዘገቡ እና ሰርተፊኬቱን ማቅረብ የሚችሉ፤
- የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ከፌደራል ወይም ከክልል መንገድ ትራንስፖርት ማቅረብ የሚችሉ
- ያላቸውን የደረጃ ጭነት መኪናዎች ዝርዝር ታርጋ ቁጥር ከነተሳቢ እና ሊብሬ (የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ) ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ከገቢዎች ጽ/ቤት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከ1-7 ተራ ቁጥር የተገለጹትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማመሳከር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ማራገፊያ ጣቢያዎች የመንገድ ሁኔታና ርቀት ከውድድሩ በፊት አስቀድመው ማየታቸውን በጽሁፍ ማረጋገጥ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ጨረታውን ካሸነፉና ውል ከፈጸሙ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የመንገድ ሁኔታ ችግር ተቀባይነት አይኖረውም።
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ዝርዝር መሰረት የአፈር ማዳበሪያ የሚጓጓዝበትን ዋጋ ለአንድ ኩንታል የአንድ ኪሎ ሜትር የማጓጓዣ ዋጋ በግልፅ ሳይደለዝ በተቀመጠው ሠንጠረዥ ላይ መሙላት አለባቸው።
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማሰከበርያ ዋስትና ከህጋዊ ባንክ የተመሰከረለት CPO በድርጅቱ ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተወዳድረው የሚያሸንፉ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው በጽሁፍ ከተገለጸላቸው ጀምሮ በ15 ቀን ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ድምር 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ርPO በማቅረብ ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 1000 ብር በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ጅማ ከተማ በሚገኘው የዩኒዬኑ ጽ/ቤት ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ማስከበሪያ ሰነድ ከ 60 ቀን በኋላ ለተጨማሪ 28 ቀን ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል።
- የጨረታው ሰነድ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ለየብቻ ተዘጋጅቶ ኦሪጅናሉን እና ፎቶ ኮፒውን በተለያየ ፖስታ አስገብተው በማሸግ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን፤ ኦሪጂናል የቴክኒካል ማስረጃዎችን ከ CPO ጋር በአንድ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ“ኦሪጅናል ቴክኒካል” ፣ ኮፒ የቴክኒካል ማስረጃዎችን ደግሞ በሌላ ፖስታ በማሸግ የታሸገበት ፖስታ ላይ “ኮፒ ቴክኒካል” በማለት፤ እንዲሁም የዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ሰነዶችን ኦሪጂናሉን በአንድ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ “ኦርጅናል ፋይናንሻል“፣ ኮፒ የዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ሰነዶችንም ለብቻ በማሸግ “ኮፒ ፋይናንሻል” በማለት በጥቅሉ በአራት ፖስታ ታሽጎ የሚቀርብ ሲሆን በተጨማሪም በእያንዳንዳቸው ፖስታ ላይ የተወዳዳሪው ስም አድራሻ; ፊርማ እና በማህተም በማረጋገጥ ሁሉንም የታሸጉ ፖስታዎች በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ አድርጎ በማሸግ የተወዳዳሪው ስምና አድራሻ፣ የዩኒዬኑ ስም ተጽፎበት በማህተም በማረጋገጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሣጥን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጥዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ቀጥሎ ባሉት የስልክ ቁጥሮች ወይም በአካል ቀርበው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
0917550748
የጅማ ገበሬዎች ሁለገብ የህብረት ሥራ ዩኒዬን
