በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ቋሚ እቃ፤ የድንኳን ኪራይ እና የሞንታርቦ ኪራይ እና የሳውንድ ሲስተም እንዲሁም የዲኮር ሥራዎች በመንግሥት በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ቋሚ እቃ፤ የድንኳን ኪራይ እና የሞንታርቦ ኪራይ እና የሳውንድ ሲስተም እንዲሁም የዲኮር ሥራዎች በመንግሥት በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ሕጋዊ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ እንዲሁም የተጫራቾች የምስክር ወረቀት ያላቸው:
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው በታሸገ ፖስታ በወረዳው ፋይናንስ ግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-1፡30 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ማለትም በየሎቱ
ሎት1 10,000.00 (አስር ሺህ ብር ብቻ)
ሎት.2 3.000.00 (ሦስት ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የእያንዳንዱ የሚወዳደሩበት ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የእቃውን ናሙና ዝርዝር ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በየሎቱ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል በወረዳ 08 በፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 24 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 24 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን እቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% (ፐርሰንት) የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከጽ/ቤቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት መፈጸም ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን እቃዎች ርክክብ የሚፈጽሙበት በራሳቸው ትራንስፖርት ሆኖ በወረዳው ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ነው፡፡
- ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ሳያሟሉ በጨረታው ላይ ለመሳተፍ መሞከር በሕግ ያስጠይቃል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡ ተጫራቾች ከአንድ በላይ ሎቶች መወዳደር ከፈለጉ የየሎቱን የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 08 የፋይናንስ ጽ/ቤት በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011 6 66 16 14 ደውለው ያነጋግሩን፡፡
አድራሻ፡- ፊጋ ሰፈር ከበሻሌ ንግድ ባንከ ወደ ሰሚት በሚወስደው አስፓልት መንገድ ሳፋሪ ት/ቤት ከመድረስዎት በፊት መሲ ሕንፃ ወረድ ብሎ፡፡
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት
