Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address , Phone: 0908191458
  • Website
  • Deadline10 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price400.00
  • Bid Security50,000
  • opening date2026-01-10 00:00:00
  • Categories Construction Materials And Raw Materials

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ጽ/ቤት እና ለአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መስሪያቤቶች ለተለያዩ ግንባታዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸው ፌሮ ብረቶችን፣ ልሙጥ እና ሽብሽብ ፓርሊን ቆርቆሮዎችን፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣ ምስማሮችን እና ሲሚንቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ጽ/ቤት እና ለአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መስሪያቤቶች ለተለያዩ ግንባታዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸው ፌሮ ብረቶችን፣ ልሙጥ እና ሽብሽብ ፓርሊን ቆርቆሮዎችን፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣ ምስማሮችን እና ሲሚንቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. በመስኩ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የተጨማሪ እሴት ተክስ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
  3. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ እና ከግብር ዕዳ ነፃ ስለመሆናቸው እንዲሁም የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፣
  4. የምዝገባ ሰርተፍኬት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000/ሃምሳ ሽህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ(CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉትን እቃ አለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ገቢ ማድረግ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ የትራንስፖርት የማስጫኛና የማውረጃን ጨምሮ በጨረታ ሰነድ ላይ መሙላት አለባቸው።
  8. አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  9. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለእቃዎቹ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400(አራት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10(አስር) በመምጣት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15(አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን በሚገባ በመሙላት 01(አንድ) ኦርጂናል እና 01(አንድ) ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15(አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባለው 16ኛው የስራ ቀን እስከ ቀኑ 6፡30 ሰዓት ድረስ በአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ ቤት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 6፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጨረቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

 ማሳሰቢያ፡-

  1. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  2. የተወዳዳሪ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን መክፈቻ ቀን አይለወጥም።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር፡- 09-08-19-14-58 ወይም 09-12-71-97- 62 ይደውሉ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender