በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ ግዥ ንብረት አስ/ቡድን በ2018 በጀት ዓመት ለወረባቦ ወረዳ ውሃና ኢነርጂ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የፋብሪካ ግንባታ እቃዎች ማለትም ለባዮ ጋዝ ግንባታ አገልግሎት የሚውል የፋብሪካ ግንባታ እቃ ሎት 1 እና ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የፋብሪካ እቃዎች፣ ሎት 2 እንዲሁም ለወረባቦ ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የፕሪንተር ቀለም፣ ሎት 3 በግልፅ ጨረታ በሎት ድምር አወዳድሮ አሸናፊዎችን በመለየት መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ ግዥ ንብረት አስ/ቡድን
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ ግዥ ንብረት አስ/ቡድን በ2018 በጀት ዓመት ለወረባቦ ወረዳ ውሃና ኢነርጂ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የፋብሪካ ግንባታ እቃዎች ማለትም ለባዮ ጋዝ ግንባታ አገልግሎት የሚውል የፋብሪካ ግንባታ እቃ ሎት 1 እና ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የፋብሪካ እቃዎች፣ ሎት 2 እንዲሁም ለወረባቦ ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የፕሪንተር ቀለም፣ ሎት 3 በግልፅ ጨረታ በሎት ድምር አወዳድሮ አሸናፊዎችን በመለየት መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች አግባብ ያለው የንግድ ስራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና የሚታይ ኮፒ በማድረግ በፖስታ አሽገው ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ከላይ በተራ ቁጥር 1 እስከ 2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ ለሚፈልጉ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከገንዘብ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ15/04/2018 ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከ 15/04/2018 እስከ 16ኛው ቀን በ30/04/2018 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በእያንዳንዱ ሎት በመለየት ኦርጅናልና ኮፒ ሁለት ሁለት ፖስታ በማዘጋጀት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በወረባቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ማለትም ፕሪንተር ቀለም በተመለከተ ከተቀመጠው ናሙና ውጭ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታው በ 16ኛው ቀን በ30/04/2018 ዓ.ም በ 5፡00 ሰዓት ይዘጋል፡፡
- ጨረታው በ 16ኛው ቀን በ30/04/2018 ዓ.ም በ 5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ሆነ ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በተጫራቾች ፊት በወረባቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 በግልጽ ይከፈታል።
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፋቸውን እቃዎች በተጠየቀው መሰረት ውለታ በመውሰድ ኦርጂናል እቃዎችን ብቻ በመለየት ወረባቦ ወረዳ እቃውን በጠየቁት ባለሙያዎች የእቃውን ጥራት በማስረጋገጥ ወረባቦ ወረዳ በየንብረት ክፍሉ ገቢ በማድረግ ገቢ ለሆኑት እቃዎች ክፍያ መውሰድ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበትን እቃ ጠቅላላ ዋጋ 2% በእያንዳንዱ ሎት በመለየት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ መሂ 1 በመቁረጥ ከጨረታ ፖስታው ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
- በመጫረቻ ሠነድ ላይ ከሰፈሩት የውል ቃሎችና ሁኔታዎች ጋር መሰረታዊ ልዩነት ያለው ሃሣብ ማቅረብ ከጨረታ ተሣታፊነት ያሰርዛል፡፡
- በሚገዛው ግዥ ላይ መ/ቤቱ 20% የመጨመር 20% የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ የተጫራች መመሪያ ሳይገነጠል አያይዞ ማቅረብ ግዴታ ነው፡፡
- በነጠላ ዋጋ ላይ ሆን ተብሎ የተጋነነ ስርዝ ድልዝ መኖር ከጨረታ ተሳታፊነት ያሰርዛል።
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ለሚወዳደሩበት አቅርቦት ተጨማሪ ማስረጃ ቢያስፈልጋቸው 033-221-00-25 ወይም በግንባር በመቅረብ ወይም በስራ ሂደቱ ቢሮ ቁጥር 4 መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
- የጨረታው መከፈቻ ቀን የበዓል ቀን፣ ቅዳሜና እሁድ ከገጠመ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ ግዥ ንብረት አስ/ቡድን
