Tender Detail

Tender Details


የዲላ ትምህርት ኮሌጅ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Dilla Polytechnic College (የዲላ ትምህርት ኮሌጅ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02/2018

 

ሀ/ የተለያዩ እቃዎችን ማለትም

  1. የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችና ተመሳሳይ፣ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3,965.00.
  2. የጽዳት ዕቃዎች፣ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 302.00.
  3. የተለያዩ መገልገያ መሣሪያዎችና ተመሳሳይ፣ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 61.00.
  4. የላብራቶሪ ዕቃዎችን፣ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3,615.00.
  5. ባለፈር ምንጣፍ፣ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 960.00 በማስያዝ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት ከላይ የተጠቀሱ እቃዎችን ዋጋ ቫትን አካቶ በመሙላት ኮሌጁ ለዚሁ ሥራ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ለ/ በዚሁ መሰረት

  1. በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር አጠናቅቀው የከፈሉ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች በ(VAT) ከፋይነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፣
  3. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው እራሣቸውን ማግለል አይችሉም፣
  4. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፣
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለሚሣተፋባቸው ዕቃዎች ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ከላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች በጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሳተፍ ይችላሉ፣
  7. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  8. ኮሌጁ በጨረታው አሸናፊ ለሆነው ድርጅት ክፍያ የሚፈጽመው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው።
  9. ተጫራቹ ለጨረታው የሚያቀርቧቸውን ሰነዶች ዋናውንና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማሸግ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የዲላ ትምህርት ኮሌጅ የግልጽ ጨረታ ቁጥር 02/2018 ዓ/ም በማለት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  10. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል። ጨረታው በ16 ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመሥሪያ ቤቱ የማኔጅመንት መሰብሰቢያ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል።
  11. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት በጨረታው ያሸነፈባቸውን እቃዎች ማንኛውም ወጪ የጉምሩክ ቀረጥን ጨምሮ በመሸፈን ዕቃዎቹን የሚያስረክበው ዲላ ትም/ ኮሌጅ ነው።
  12. ተጫራቾች ለጨረታ በሠነድ ላይ ያቀረቡት ዋጋ ላሸነፋባቸው ቋሚና አላቂ ዕቃዎች እስከሚያስረክቡበት ጊዜ ድረስ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
  13. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና 10% በማስያዝ ከመሥሪያ ቤቱ ጋር የሽያጭ እና የግዥ ውል ይፈራረማሉ።
  14. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ የዕቃዎቹን አይነት፣ የአምራቹን ስም፣ የተመረተበት ሀገር፣ የሞዴል ቁጥርና የተመረተበትን ዓመት ጭምር ማካተት ይኖርበታል። የእስፔስፊኬሽን መግለጫ የሚያስፈልጋቸው እቃዎች በአይነት በፎቶና የአቅም መለያ እንደ አማራጭ ይቅረብ።
  15. ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፣
  16. የዕቃው ርክክብ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር የሚከናወነው የግዥው መሥሪያ ቤት ባለሙያዎች በሚያደርጉት የጥራትም ሆነ የዓይነት ምርመራ በ /Specification/ መሠረት ትክክለኛነቱ ሲረጋገጥ ይሆናል፣
  17. የጨረታ ሰነዱን ከዲላ ትምህርት ኮሌጅ ብር 100 በመክፈል ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር በግዥ ማግኘት ይችላሉ።
  18. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ እንዲሁም ብዛት የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።

 

ለበለጠ መረጃ

የዲላ ትምህርት ኮሌጅ ስልክ ቁጥር 046-331-36-29

የዲላ ት/ኮ/ግ/ፋ/ን አስተዳደር ስልከ ቁጥር 046-331-42-51

ፋክስ 046-331-24-92

 

የዲላ ትምህርት ኮሌጅ

 

Save Tender