Tender Detail

Tender Details


በማዕ/ኢ/ክ/ቴ/ሙ/ት/ሰ/ቢሮ ሳጃ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት ለኮሌጁ እና የሚውል ዕቃዎችን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በማዕ/ኢ/ክ/መ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ቢሮ ሳጃ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በማዕ/ኢ/ክ/ቴ/ሙ/ት/ሰ/ቢሮ ሳጃ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት ለኮሌጁ እና የሚውል ዕቃዎችን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

 

ተ.ቁ

የዕቃው ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ Bid Bond /Cpo/

1

የአይ ሲ ቲ ዲ/ት /ICT/ ሥልጠና መሳሪያዎች

5,000

2

የኤሌክትሮኒክስ ዲ/ት ሥልጠና ዕቃዎች

5,000

 

የሥራ ፍቃድ እና የዘመኑን የሥራ ግብር አጠናቆ የከፈሉበት ማስረጃ የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የንግድ መለያ ቁጥር ጨምሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

  1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ለ15 የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት የም ዞን ሳጃ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአካል በመምጣት ወይም በተወካይ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ/ በመክፈል ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዋጋ ማቀረቢያ ሰነድና ሌሎች ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕና የጨረታውን ስምና ቁጥር በመጥቀስ ከ13/04/2018 ዓ.ም እስከ 1/05/2018 ዓ.ም ድረስ ከ11፡30 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መጨመር ይኖርባቸዋል።
  3. ጨረታውን በ2/5/2018 ዓ.ም በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ ይከፈታል።
  4. ኮሌጁ የተሻለ ሁኔታ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  5. አሸናፊ ከተረጋገጠ በኋላ ወዲያውኑ ሌሎች ያስያዙት ዋስትና ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ይመለሳል።
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብና ዋጋ ታክስን የሚያካትትና የማያካትት መሆኑን በትክክል መግለጽ አለበት።
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሀሳብና ዋጋ ላይ ፊርማቸውን፣ ቀን እና የድርጅቱ ማህተም ማሳረፍ ይኖርባቸዋል።
  8. አሸናፊ ተጫራች አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ በውሉ መሰረት ማጠናቀቃቸውን ከተረጋገጠ በኋላ ሙሉ ክፍያ ይከፈላቸዋል።
  9. የጨረታው መክፈቻ በበዓላትና በእረፍት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ላይ ይሆናል።
  10. የተጫራቾች ያለመገኘት የጨረታውን የመክፈት ሂደት አያስተጓጉልም።
  11. በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  12. ተጫራቾች የሥራ ፍቃዳቸው ያልተሟላ መረጃና በሥራ ዝርዝሩ ሰነድ ላይ የሚሞሉት የነጠላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፣ የመወዳደሪያ ዘዴ በዓይነት ይሆናል፤
  13. በአነስተኛና ጥቃቅን አዋጅ መሰረት የተደራጁ ማህበራት ከአደራጁ መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤና የቁጠባ ካፒታል ከባንክ ወይም፣ ከኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  14. ጨረታውን ያሸነፈ አቅራቢ እስከ የም ዞን ሳጃ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ድረስ ዕቃውን ማቅረብ ይኖርበታል፤
  15. የመወዳደሪያ ቋንቋ በአማርኛ ሲሆን የግዥ ጠያቂ ኮሌጁ የሚፈልገውን ዝርዝር ዕቃ ሙሉ በሙሉ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፤
  16. የሥራው ቦታ የም ዞን ሳጃ ከተማ ሲሆን ከአዲስ አበባ 240 ኪ.ሜ ወደ ጅማ በሚወስደው መንገድ ላይ ትገኛለች፤
  17. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09 24 38 82 27/ 09 17 06 16 87 ደውሎ ማግኘት ይችላሉ።

 

የሳጃ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

Save Tender