በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የአዝርዕት ላብራቶሪ ማዕከል ጥገና እና የሆቴሎች መስተንግዶ በሀገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የአዝርዕት ላብራቶሪ ማዕከል ጥገና እና የሆቴሎች መስተንግዶ በሀገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን ነጥቦች ማሟላት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ግዴታ ማሟላት ያለባቸው የቅድመ መወዳደሪያ መስፈርቶች ማለትም፡-
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሠ ንግድ ፈቃድ
- የንግድ ብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ያለው
- ንግድ ፈቃድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
- ሲ.ፒ.ኦ
- የጨረታ ሰነድ ግዥ የፈጸመ እና
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያለው ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ በአፋር ብሔራዊ ከ/መ/ የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ ተጫራቾች ወይም የሕጋዊ ወኪል ፈርማና ማህተም ማኖር ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ ለውድድር የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 1% በሲፒኦ (CP.O) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ከተሸነፈ ለዋስትና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታው ውጤት ታውቆ ውል ከተፈራረሙ በኋላ ወዲያውኑ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት የውል ማስከበሪያ ይመለስላቸዋል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርቡትን የውድድር ጥያቄ መ/ቤቱ አይቀበልም።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰአት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በዕለቱ 4፡30 ሠአት በአፋር ብሔራዊ ከ/መ/እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በቢሮው ስልክ ቁጥር 033-366-60-22 ወይም 033-366-33-76 ደውለው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ /ሰመራ/
