በአራዳ ክ/ከተማ የወረዳ 09 ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የመንግስት ንብረት አስተዳደር ከተለያዩ ቦታዎች የፈረሱ ላሜራዎች ቁርጥራጭ ቆርቆሮዎችና የተለያዩ ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በአራዳ ክ/ከተማ የወረዳ 09 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
(2018 ዓ.ም)
በአራዳ ክ/ከተማ የወረዳ 09 ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የመንግስት ንብረት አስተዳደር ከተለያዩ ቦታዎች የፈረሱ ላሜራዎች ቁርጥራጭ ቆርቆሮዎችና የተለያዩ ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች 5000.00 አምስት ሺህ ብር CPO በማስያዝ የጨረታውን ሰነድ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል የመወዳደሪያ ዋጋችሁን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታው መክፈቻ ቀን በ16ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት በወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የሚከፈት መሆኑን እየገለፅን። ወረዳው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አራት ኪሎ ብርሃንና ሰላም ወረድ ብሎ ሲፒዩ ኮሌጅ ፊት
ለፊት ሲሆን ለበለጠ መረጃ በአካል ቢሮ ድረስ በመምጣት መጠየቅ የምትችሱ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃልን።
ስልክ ቁጥር 0118684783
በአራዳ ክ/ከተማ የወረዳ 09 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት
