Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ግዥ፤ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት /ታርጫ/
  • Address ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0914274390
  • Website
  • Deadline08 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityለሎት 1 ለተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 80,000 (ሰማኒያ ሺ)፤ ሎት 2 ለተሸከርካሪ ሞተር ግዥ 20,000 (ሃያ ሺ) ብር፣ ለሎት 3 ጀነሬተር 40,000 (አርባ ሺ) ብር
  • opening date2026-01-09 00:00:00
  • Categories Generators , Electronics Materials , Vehicle Spare Parts

ደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ በ2018 በጀት ዓመት ለቴሌቪዥን አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ የተሽከርካሪ (ሞተር) እና ጀነሬተር ግዥ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾችን በመጋበዝ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ግዥ፤ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት /ታርጫ/


 

በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የመ/ቤቱ ሥም : ደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ (ደምሚኔ)

የጨረታ አይነት : ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የጨረታ ቁጥር : 007/2018፤ 008/2018፤ 009/2018   

 

ደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ በ2018 በጀት ዓመት ለቴሌቪዥን አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ የተሽከርካሪ (ሞተር) እና ጀነሬተር ግዥ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾችን በመጋበዝ አወዳድሮ እንደሚከተለው በሎት በመከፋፈል እስከ በጀት ዓመቱ ማብቂያ ማለትም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ለመግዛት ይፈልጋል።

 

ተ/ቁ

ሎት

 

1

ሎት 1

የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዢ 007/2018

2

ሎት 2

የተሸከሪካሪ (ሞተር) ግዥ 008/2018

3

ሎት 3

ጀኔሬተር ከኤትኤስ ጋር (Generator with ATS) 009/2018

 

በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ አቅራቢነት ሰርተፍኬት፤ የቲን (Tin) እና የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. በፈዴራል ግዥ አስተዳደር ባለሥልጣን በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ለተከታታይ 15 ቀናት በደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 5 የጨረታ ሰነዱን መውሰድ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይንም ጥሬ ገንዘብ ወይንም ሕጋዊ የባንክ ቼክ ለሎት 1 ለተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 80,000 (ሰማኒያ ሺ)፤ ሎት 2 ለተሸከርካሪ ሞተር ግዥ 20,000 (ሃያ ሺ) ብር፣ ለሎት 3 ጀነሬተር 40,000 (አርባ ሺ) ብር በደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ስም በማሠራት ከጨረታ ሰነድ ጋር በማዘጋጀት አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዕቃ ዝርዝር ዋጋ በየሎቱ በመከፋፈል እና የሎት ቁጥሩን ሠነዱ ላይ በመጻፍ የአንዱ ዋጋ ከቫት በፊትና ከቫት በኋላ በማለት ምንም ዓይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በሰም (በሙጫ) በታሸገ ኢንቬሎፕ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል የጨረታ ዶክመንት ተገቢውን ፊርማ እና ማኅተም በማሳረፍ ለየብቻ ኦርጅናልና ኮፒ በታሸጉ ፖስታዎች በማዘጋጀት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርከ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 5 ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች መ/ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን በቀረበው ሎት መሠረት ፖስታ ላይ መግለጽ ይኖርባቸዋል።
  8. ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት እስከ መሥሪያ ቤቱ ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ዕቃዎችን ማቅረብ ይኖርበታል።
  9. የጨረታው ሳጥን በ15ኛው ቀን ከሰዓት 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛ ቀን ከጧቱ 3፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  10. ከተራ ቁጥር 1 ጀምሮ የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶችን ያሟሉ ተጫራቾች ብቻ ወደ ፋይናንሻል ውድድር ይቀርባሉ።
  11. አሸናፊው ማሸነፉን ሲረጋገጥ ያሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ /performance bond/ ማስያዝ አለበት።
  12. አሸናፊው ማሸነፉ ከተገለጸበት ጀምሮ 7 (ሰባት) የሥራ ቀናት ውስጥ ውል መግባት አለበት።
  13. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል። በመክፈቻው ዕለት የተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች ያለመገኘት የጨረታ መከፈት ሂደትን አያስተጓጉልም።
  14. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

በተጨማሪ መረጃ፡ 0914274390 /0907560537 ይደውሉ።

 

የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ግዥ፤ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት /ታርጫ/

Save Tender