Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የበሻሻ-ጌራ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት
  • Address ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0922195634
  • Website
  • Deadline29 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • Bid Security100,000 (አንድ መቶ ሺ) ብር
  • opening date2025-12-29 00:00:00
  • Categories Vehicles Rent

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የበሻሻ ጌራ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የሰርቪስ ባስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የበሻሻ-ጌራ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት


 

የሰርቪስ ባስ ኪራይ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የበሻሻ ጌራ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የሰርቪስ ባስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ የትራንስፖርት ማህበራት አከራይ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው።

  1. አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ሰርተፊኬት፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ማስረጃ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆን ይኖርበታል።
  2. የባለቤትነት መታወቂያ (ሊብሬ) ያለው ወይም ህጋዊ ውክልና፣
  3. የሶስተኛ ወገን ሽፋን የሚያቀርብ፣
  4. የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ፣
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ) CPO ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት በመ/ቤቱ አስተዳደርና ፋይናንስ ክፍል የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ) ከፍለው የጨረታ ሰነዱን ከግዥ አቅርቦትና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ሰርቪስ ባስ እና ሚኒባስ መኪኖች በቀን የሚከራይበትን ዋጋ ለመሙላት በሻሻ ጌራ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ቢሮ በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነድ በመውሰድ ዋጋ ከሞሉ በኋላ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።
  8. አሸናፊ ተጫራቾች የቴክኒክ ምርመራውን ካለፉ ውል በመፈፀም ወዲያውኑ ወደ ሥራ መሰማራት አለባቸው።
  9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ጠዋት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የበሻሻ-ጌራ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ቢሮ /የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ዕለት የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ቀን ይከፈታል፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።

 

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የበሻሻ ጌራ መንገድ ግንባታ ፕሮጀከት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተዘረዘሩትን ሰርቪስ ባስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡

 

ተ.ቁ

የመሣሪያው አይነት

መለኪያ

ብዛት

የኪራይ ዋጋ ነዳጅና ተ.እ.ታክስ ጨምሮ ብር በቀን በተጫራቾች የሚሞላ

1

አይሱዙ ሰርቪስ ባለ >24 ሰው መጫን የሚችል

ቁጥር

1

የኪራይ ዋጋ

 

 

 

2

ሚኒባስ >12 ሰው መጫን የሚችል

 

2

 

 

ማሳሰቢያ፡- ለአይሱዙ ሰርቪስ ባስ እና ለሚኒባሶች የስሪት ዘመናቸው እ.ኤ.አ ከ2000 ጀምሮ ያሉትን መጠቀም የሚቻል ሲሆን

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0922195634/0911807247

 

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የበሻሻ-ጌራ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት

 

Save Tender