በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የዓለም ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት በ2018 በጀት ዓመት ለ2ኛ ዙር ጨረታ ለመኖሪያ እና ንግድ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል።
የዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

- በመሆኑም መጫረት ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እና በኢትዮጵያ ሬዲዮ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ይሆናል።
- ጨረታው የሚዘጋው በአስረኛው ቀን 11፡30 ላይ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን 3፡00 ላይ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ በተመለከተ በዓ/ከ/ከ/አስ/መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በዓ/ክ/ከ/አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታውን ዝርዝር መረጃ በጽ/ቤቱ የውስጥ ማስታወቂያ መለጠፊያ ሰሌዳ ላይ የሚገለፅ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ዓለም ከተማ ስልክ ቁጥር 011 1320 090
የዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት