Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስ/ትምህርት ቢሮ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ኦዳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address ከቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ዝቅ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline29 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያው መጠን በዕጣ ይለያያል።
  • opening date2025-12-29 00:00:00
  • Categories Electrical And Electromechanical , Furniture , Educational And Training Equipment And Machinery

በአዲስ አበባ ከተማ አስ/ትምህርት ቢሮ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ኦዳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስ/ትምህርት ቢሮ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ኦዳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር ኦዳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት/002/2018 ዓ/ም

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስ/ትምህርት ቢሮ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ኦዳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ጨረታውን ለማሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው።

ሎት ቁጥር         የሎት ዝርዝር               የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮ.ብር

ሎት 4………አላቂ የትምህርት እቃዎች /ኬሚካሎች……. 5500 (አምስት ሺ አምስት መቶ ብር) ብቻ

ሎት 6………………. ልዩ ልዩ መሳሪያዎች…………………………………4,000 (አራት ሺ ብር) ብቻ

ሎት 9………………. የኤሌክትሮኒክስ ቋሚ እቃዎች……………….....19,000 (አስራ ዘጠኝ ሺ ብር) ብቻ

ሎት 10……………. ተገጣጣሚ የፈርኒቸር እቃዎች…………………9,100 (ዘጠኝ ሺ አንድ መቶ ብር) ብቻ

  1. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከፋይናንስ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ በራሳቸው ምርት ብቻ ካደራጃቸው ጽ/ቤት የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና ደብዳቤ በማፃፍ መወዳደር ይችላሉ።የራሳቸው ምርት ካልሆነና ገዝተው ለሚያቀርቡት እቃ የጨረታ ሰነድ መግዥያ የጨረታ ማስረከቢያ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ፋይናንስ ቢሮ በመምጣት ዋጋ የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  4. ጨረታው በአስረኛው ቀን 10፡00 ሰዓት ታሽጎ በአስራ አንደኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  5. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
  7. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉበትን እቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ት/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
  8. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. የጨረታ ሰነዱን በትክክል በማንበብና በመሙላት ማህተምና ፊርማ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ በማድረግ ዋጋ መሙለት ሎቱን ብቻ ቀዶ በማውጣት መሙላት ከጨረታው ውድቅ ያደርጋል ስለዚህ የጨረታ ሰነዱ ሁሉም በስርዓት በመሙላት ገቢ መሆን አለበት።
  10. ዋጋው ከነቫቱ መሞላት ይኖርበታል።
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡- ከቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ዝቅ ብሎ

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስ/ትምህርት ቢሮ

በቦሌ ክ/ከተማ የኦዳ 2ኛ አጠቃላይ ደረጃ ት/ቤት

Save Tender