Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የመቐለ ሪጅን ጽ/ቤት
  • Address በመቐለ ከተማ ፕላኔት ሆቴል ወረድ ብሎ የሚገኝ ዛምራ ህንፃ ላይ የመቐለ ሪጅን ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ሳፕላይ ቼይን ንብረትና ጠ/አ ቢሮ ቁጥር 304፡ ትግራይ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251342406712
  • Website
  • Deadline02 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያው የገንዘብ መጠን በየ ሎቱ የተለያየ ነው።
  • opening date2026-01-02 00:00:00
  • Categories Electrical And Electromechanical , Metals And Metal Working , Electrical Materials

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት ንብረት የሆኑት የተለያዩ ያገለገሉ ብዛታቸው ከ150 በላይ ትራንስፎርመሮች ባሉበት ሁኔታ እንዲሁም የተለያዩ የተጓደሉ የትራንስፎርመሮች አካላት በብረት መልክ ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የመቐለ ሪጅን ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር መቐ/ሪ/ን/ማ/04/2018 ሎት -4

 

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት ንብረት የሆኑት የተለያዩ ያገለገሉ ብዛታቸው ከ150 በላይ ትራንስፎርመሮች ባሉበት ሁኔታ እንዲሁም የተለያዩ የተጓደሉ የትራንስፎርመሮች አካላት በብረት መልክ ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም በትራንስፎርመር ማምረትና ጥገና እና በብረታ ብረት ምርቶች በማምረትና ማቅለጥ ንግድ ሥራ የተሰማሩና ንግድ ፈቃድ ያላቸው ብቻ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የመቐለ ሪጅን 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 302 ላይ ቀርበው የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ/ ከፍለው የሚወገዱትን ንብረቶች ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ገዝተው ዘወትር በሥራ ቀናት ከታኅሳስ 09/2018 ዓ.ም እስከ ታኅሳስ 24/2018 ዓ.ም ጠዋት 4:00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ሰነድን የገዙበት ደረሰኝ ይዘው ትራንስፎርመሮቹ በሚገኙበት ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት ለመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት” (MEKELLE REGION ELECTRIC UTILITY) ተከፋይ የሆነ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Security) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰዳቸውን እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ስማቸውን እና ጨረታ ቁጥሩን (መቐ/ሪ/ን/ማ/04/2018 ሎት-4) በመግለፅ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እስከ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ብቻ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  5. ጨረታው ታኅሳስ 24/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመቐለ ከተማ ፕላኔት ሆቴል ወረድ ብሎ የሚገኝ ዛምራ ህንፃ ላይ የመቐለ ሪጅን ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ሳፕላይ ቼይን ንብረትና ጠ/አ ቢሮ ቁጥር 304 ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
  7. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0342406712 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  8. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የመቐለ ሪጅን ጽ/ቤት

 

Save Tender