ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋይናንስ/ጽ/ቤት የወረዳው ንብረት ለሆነው ግሬደር ማሽን የሚሆን ጎማ ከአቅራቢዊች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋይናንስ/ጽ/ቤት የወረዳው ንብረት ለሆነው ግሬደር ማሽን የሚሆን ጎማ ከአቅራቢዊች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት በጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- በዘርፋ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቀረብ የሚችል።
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል /የምትችል።
- የዘመኑን ግብር የከፈለ/ለች እና ክሊራንስ ከግብር መ/ቤት ያቀረበ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል /የምትችል
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆን እና ኮፒዉን አያይዞ ማቀረብ የሚችል/የምትችል።
- ተጫራቾች ከጨረታ ስነዶች ጋር የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በአሃዝ እና በፊደል መግለጽ አለባቸው:: በፊደል እና በአሃዝ መካከል ልዩነት ካለው በፊደል የተገለጸው ይወሰዳል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ሁለት መቶ (200) በመክፍል ከደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢ/ ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1O/አስር/ በአካል በመቀረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል አንድ (1) ኦርጅናል እና ሁለት(2) ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል አንድ() ኦርጅናል እና ሁለት(2) ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ማቀርብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡ ያለበለዚያ ያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ፖስታውን በደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ለዚህው ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10(አስር) ቀናት ክፍት ሆኖ በ10ኛው ቀን ከሰዓቱ 9:00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከቀኑ 9:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡
- ተጫራቾች የማህበሩ አባላት ስለመሆናቸዉ የስም ዝርዝር ከነ ሥራ ሀላፊነታቸዉ የሚገለጽ ከአደራጅ መ/ቤት ለደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ/ጽ/ቤት አድራሻ የተጻፈ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል።
- የግንባታ ዲዛይን የሚቀርብ ይሆናል
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
አድራሻ፡- የደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ደ/ወርቀ ስልክ፡- 0966 886 973 / 0910 997 747/0929 241 731 በመደወል መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋይናንስ/ ጽ /ቤት
