Tender Detail

Tender Details

  • Company Belayab Motors (በላይአብ ሞተርስ ኃ.የተ.የግል ማህበር)
  • Address ቃሊቲ ብሔራዊ ት/ቤት ጀርባ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114 343691
  • Websitehttps://www.belayabmotors.com
  • Deadline30 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security50,000.00
  • opening date2025-12-30 00:00:00
  • Categories Vehicle

በላይአብ ሞተርስ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ማለትም የሲኖ ትራክ(si no Truck): የኒሳን ዩዲ (Nissan UD): የኪያ(KIA): የፉቶን ዳምፕ ትራክ (Foton Dump Truck ፎርክሊፊት (Forlift)፣ የሎደር (Loader) የኤክስካቫተር(Excavator)፣ የሪዮት ኮንትሮል (Riot Control) የዳምፐር(Damper)፣ የዜድ ኤን ኤ ፒክ አፕ (ZNA pick up)፣ ሪች (Rich)፣ ቢሾፍቱ ፒክ አፕ(Bishoftu pick up): የፎቶን ፒክ አፕ (foton pick up): የፎርላንድ: (Forland): የፋዋ ቤላ (FAW BELLA)፣ የአቲንግ(Oting)፣ የፎቶን ሚኒባስ(Foton minibus)፣ ሙዳን ባስ(Mudan Bus) ኤፍኤሰር(FSR)፣ጋርቤጅቲፐር(Garbage Tipper)፣ ካኒባላይዝ(Canibalize) እና ዎኪንግ ትራክተር(Walking Tractor)፣ መለዋወጫዎችን(Spare parts) በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Belayab Motors (በላይአብ ሞተርስ ኃ.የተ.የግል ማህበር)


የጨረታ ማስታወቂያ

በላይአብ ሞተርስ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ማለትም የሲኖ ትራክ(si no Truck): የኒሳን ዩዲ (Nissan UD): የኪያ(KIA): የፉቶን ዳምፕ ትራክ (Foton Dump Truck ፎርክሊፊት (Forlift)፣ የሎደር (Loader) የኤክስካቫተር(Excavator)፣ የሪዮት ኮንትሮል (Riot Control) የዳምፐር(Damper)፣ የዜድ ኤን ኤ ፒክ አፕ (ZNA pick up)፣ ሪች (Rich)፣ ቢሾፍቱ ፒክ አፕ(Bishoftu pick up): የፎቶን ፒክ አፕ (foton pick up): የፎርላንድ: (Forland): የፋዋ ቤላ (FAW BELLA)፣ የአቲንግ(Oting)፣ የፎቶን ሚኒባስ(Foton minibus)፣ ሙዳን ባስ(Mudan Bus) ኤፍኤሰር(FSR)፣ጋርቤጅቲፐር(Garbage Tipper)፣ ካኒባላይዝ(Canibalize) እና ዎኪንግ ትራክተር(Walking Tractor)፣ መለዋወጫዎችን(Spare parts) በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ እቃዎቹ አዲስ አበባ እና አዳማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ይገኛሉ፡፡ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

1. የጨረታ ስነዱን የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመግዛት ዋጋቸውን በመሙላት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡

2. ጨረታው የሚቆየው ጋዜጣው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ሲሆን በ11ኛው ቀን 4፡00 ተከፍቶ 4፡30 ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሳሪስ ቀይ መስቀል ወስጥ በሚገኘው በላይአብ ሞተርስ ይከፈታል፡፡

3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የተለያዩ መለዋወጫ እቃዎች ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) በባንከ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ድርጅቱ ባወጣው የመነሻ ዋጋ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች ሰነድ ከገዙ በኋላ ቃሊቲ ብሔራዊ ት/ቤት ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በመቅረብ የእቃዎቹን ናሙና በአካል ማየት ይችላሉ፡፡

6. አሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከፍሎ በ15 ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል።

7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8. ማንኛውም ተጫራች የሚፈልገውን የመለዋወጫ ብዛት በተናጠል መጫረት ይችላል፡፡

9. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

ከላይ በተዘረዘሩት መስፈርት ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች ሰነዱን ሳሪስ ካዲስኮ ዋና መስሪያ ቤት የበላይአብ ሞተርስ ግቢ ውስጥ መውሰድ ይችላሉ፡፡

አድራሻ፤

በላይአብ ሞተርስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር

ሞባይል: - 0966215183/84

ስልክ፡-0114 343691 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በላይአብ ሞተርስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር

Save Tender