Tender Detail

Tender Details

  • Company የቤ/ጉ/ክ/መ/ ስፖርት ኮሚሽን
  • Address , Phone: 0910 024 089
  • Website
  • Deadline31 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price400.00
  • Bid Security20,000
  • opening date2025-12-31 00:00:00
  • Categories Sport Materials And Sportswear

የቤ/ጉ/ክ/መ/ ስፖርት ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት ለሚውል ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖርት ትጥቅ፣ ቁሳቁስ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የቤ/ጉ/ክ/መ/ ስፖርት ኮሚሽን


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/ስፖ/ግ/2018

 

የቤ/ጉ/ክ/መ/ ስፖርት ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት ለሚውል ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖርት ትጥቅ፣ ቁሳቁስ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ለዚሁም ተጨራቾች ቀጥሎ በተመለከተው መስፈርት መሠረት ጨረታውን መግዛት ይችላሉ።

ስለሆነም

  1. ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
  1. ተጫራቾች በጨረታው ለማወዳደር በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የአቅራቢነት የግብር ሠርተፍኬት በክልል(በፌዴራል) ደረጃ የተመዘገቡበት፤ የተጫማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት መለያ ቁጥር ሠርተፍኬት ያለቸውና ከጨረታ ውድድር ያልታገዱ መሆን ይገባቸዋል።
  2. ተጨራቾች የጨረታው ሠነድ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ከኢ.ፊ.ዴ.ሪ ባህልናስፖርት ሚኒስቴር ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ የማይመለስ ብር 400(አራት መቶ የኢትዮጵያ ብር) በመክፈል የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶችንና የሚወዳደሩበትን የአንዱን ዕቃ ነጠላ ዋጋ ከቫት በፊትና በኃላ ያለውን በትክክል በማስላት በአንድ ኦርጅናል እና በሁለት ኮፒ 1 እና 2 በማለት ለያይተው በየውስጥ ገጾች እና በየፖስታው ጀርባ በድርጅቱ ህጋዊ ሥልጣን ባለው አካል አጭር ፊርማና ክብ ማህተም በማሳረፍ በሰም በታሸገው ኤንቨሎፕ አሽገው ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዉስጥ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
  4. ተወዳደሪ ድርጅቶች ለሚወዳደሩበት እቃ ናሙና ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በሚቀጥለው ቀን 04:00 ባለው ጊዜ ይዘው በማቅረብ ማስረከብ አለባቸው :: በባህርያቸው ክብደት ያላቸውን ዕቃዎች በየስቶካቸው ማሳየት ይችላሉ፤
  5. 5, ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት አንስቶ በተከታታይ ቀናት በሚቆጠር በአስራ ስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ ልክ 4፡00 ላይ ወድያው 4፡30 ላይ ይከፈታል:: ዕለቱ የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከናወናል:: የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኃላ የሚቀርብ የጨረታ ሠነድ ተቀባይነት የለውም።
  6. ተጫራቾች ከጨረታ ሠነዱ ጋር ተያይዞ የሚሰጣቸውን የተጨራቾች መመሪያን ማንበብና መተግበር አለበቸው።
  7. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ጨረታ 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) ህጋዊ ሰውነት ካለው ባንክ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው :: የሚዘጋጀዉ ሲፒኦ ለስፖርት ትጥቅና ቁሳቁስ ግዥ ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ስም ይሆናል:: ውድድሩ እንዳበቃ ለተሸናፊ ድርጅቶት ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል።
  8. አሸናፊ ድርጅቶች ባሸነፉበት ጠቅላለ ዋጋ የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ 10% ማስያዝ ይገባቸዋል:: አሸናፊ ድርጅቶች በመንግስት የግዥ መመሪያ መሠረት የሽያጭ አገልግሎት ዋጋን መከፈል ይገባቸዋል።
  9. አሸናፊ ድርጅቶች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ 7ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ውል መግባትና ውል በገቡ በ15 ቀናት ውስጥ ዕቃዎቹን ሙሉ በሙሉ ማስረከብ አለባቸው።
  10. የመንግስት ግዥ አዋጅ እና መመሪያዎች ግዴታቸውን በማይወጡት አሸናፊ ተጫራቾች ላይ ተፈፀሚ ይሆናል።
  11. አሸናፊ ድርጅቶች ባቀረቡትና ተቀባይነት ባገኘው ናሙናና አሸናፊ በሆኑባቸው ዕቃዎች ዓይነት ፣ ጥራትና መጠን ጠብቀው ማቅረብ አለባቸው።
  12. የክፍያ ሁኔታ በሚመለከት ቢሮው ዕቃዎቹን እንደተረከበ በትራንስፈር፣ በቼክ፣ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወድያውኑ ለየድርጅቶቹ ክፍያን ይፈጽማል:: በዚህ ጨረታ የቅድመ ከፊያ ጥያቄ ማቅረብ አይቻልም ::የማስረከቢያው ቦታ አ/አበባ ሰሜን ሆቴል አከባቢ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ፊት ለፊት ዮናታን ፔንስዮን/ብርሃኑ ሆቴል ላይ ይሆናል።
  13. በነጠላና በድምር ዋጋ መካከል ልዩነት ቢፈጠር የነጠላ ዋጋ ግዥ ይሆናል።
  14. ስርዝ ድልዝ ያለበት ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም።
  15. ጨረታውን የሚፈርመው አካል ወኪሉ ከሆነ የውክልና ደብዳቤ መያያዝ አለበት።
  16. የጨረታ ዋጋ የጨረታው ውድድር ከተጠናቀቀ በኃላ ለስድስት ወር ጸንቶ ይቆያል።
  17. ማንኛውም ተጨራች በሌላ ተጫራች በተሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
  18. ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ 057 775 2431 እና 0910 024 089 /0917 183 866 መጠቀም ይችላሉ።
  19. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የቤ/ጉ/ክ/መ/ ስፖርት ኮሚሽን

Save Tender