በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ጎንደር ዞን የደባርቅ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገ/ጽ/ቤት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች ሎት1. ቧንቧና የቧንቧ መገጣጠሚያ በሎት /ምድብ/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የደባርቅ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ጎንደር ዞን የደባርቅ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገ/ጽ/ቤት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች ሎት1. ቧንቧና የቧንቧ መገጣጠሚያ በሎት /ምድብ/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሱ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሠ የንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት/ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት /TIN No/ ያላቸው
- የግዡ መጠን ብር ከ200,000 እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ /Vat Register/ የሆነ/ች የሚገዛው ዕቃ ቧንቧና የቧንቧ መገጣጠሚያ እቃው ዋጋ ከ20,000 ብር በላይ ከሆነ የቅደመ ክፍያ /Withhold tax/ 3% ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ /የሆነች/፣ ለሚገዛው ዕቃ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- የሚገዙ ዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል። እንዲህም በስፔስፊኬሽኑ መሰረት ናሙና ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ደባርቅ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከሚወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ /Bid bond/ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ከወጣበት ከ6/4/2018 ዓ/ም እስከ 5/5/2018 ዓ/ም ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይኖርባችኋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆኑ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ እና ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ተለይቶ በጥንቃቄ መታሸገ አለበት። የታሸገ ፓስታ በደባርቅ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በገ/ግ/ፋ/ን/ ስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 በ6/5/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታ በሚከፈትበት ቦታ ቀንና ሰዓት በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ የጨረታው ፖስታ እንዲከፈት ይደረጋል፡፡
- ማንኛውም አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ የእሸነፈውን ዕቃ ደባርቅ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ወጭ ማቅረብ የሚችል፤
- ጽ/ቤቱ ቧንቧና የቧንቧ መገጣጠሚያ ዕቃ ናሙና ማየት ስለሚፈልግ 6/5/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ናሙና ማቅረብ የሚችል ሆኖ ናሙና ለማቅረብ አስቸጋሪ የሆኑትን በተለይ ለትራንስፖርት ምቹ የማይሆኑትን ዕቃዎች ጽ/ቤቱ በሚያቀርበው ናሙና እና በእስፔስፊኬሽን መሰረት ይሆናል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተጠቀሰው ዕቃ 20 በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብት አለው።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0581170139 የሞባይል ቁጥር 0921535111፤ 0901441719 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የደባርቅ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት
