የአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ የ2018 በጀት አመት የ1ኛ ዙር አገልግሎት የሠራተኛ ክበብ እና የሠራተኞች አሻራ ማሽን እና ሴኩሪቲ ካሜራ በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።
በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 አፍንጮበር ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ.ጤ.ጣ 01/2018
የአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ የ2018 በጀት አመት የ1ኛ ዙር አገልግሎት የሠራተኛ ክበብ እና የሠራተኞች አሻራ ማሽን እና ሴኩሪቲ ካሜራ በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እና ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር ሰነዱን ብር 150.00 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰአት ታሽጎ በዛው እለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
- የጨረታ ማስረከቢያ ብር ከዋጋው የተሞላው 2% ከባንክ በተመሰከረ CPO ማስያዝ አለባቸው መሉ ዝርዝር መረጃው ከሰነዱ ላይ መመልከት አለባቸው፡፡
- ከገዙት ጨረታ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም
- በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር ከፋይ
- የጨረታው ዝርዝር በየአንዳንዱ ላይ ዋጋው ይሞላ
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱን የተጠበቀ ነው
- ተጫራቾች በታሸገ ፖስታ ማስገባት አለባቸው
- ተጫራቾች ለመወዳደር የሥራዉን አይነት በቦታው ተገኝተው ማየት ይኖርባቸዋል።
አድራሻ፡- አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ ከሰሜን ሆቴል ጀርባ ሲ.ሲ ኤፍ ግቢ አጠገብ
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 01111-26-52-9 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 አፍንጮበር ጤና ጣቢያ
